ስቶክሆልም (cakaaranews) ሰኞ፤ሚያዝያ 1ቀን ፤ 2010ዓ.ም በስዊድን ሀገር የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዲያስፖራ ኮሙኒቲ አባላት በተለይ የሊባን ዞን ተወላጆች በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት ንግድ፤ትራንስፖርትና እንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ፤ የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ከደር አብዲ ኢስማኢል የሚመራ የዲያስፖራና የክልሉ መንግስት ጥምር ልዕኳን ቡዱን በስቶክሆልም ከተማ ደማቅ አቀባበል እና የእራት ግብዣ እንደተረገላቸው ተገለጸ።
በተያያዜም በኢ.ሶ.ክ.መ.የንግድ፤ትራንስፖርትና እንዱስተሪ ቢሮ ኃላፊና የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት ድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ከደር አብዲ የሚመራ ጥምር ልዕኳን ቡዱኑ በስዊድን ስቶክሆልም የሚኖሩ የሊባን ዞን ዲያስፖራ አባላት በክልሉ እየተከናወነ ያለው ዘርፈብዙ የሰላም፤የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ሁሌም መደገፋቸውን ለልዑኳን ቡዱኑ ገልጸዋል።በተጨማሪም ለልዕኳን ቡዱኑ በተደረገው ደማቅ አቀባበልና ልዩ የእራት ግብዣ የቡድን መሪው የላቀ ምስገናን አቅርበዋል።