አብዛኛው የክልሉ አከባቢዎች ቆላማና በረሃማ እንደመሆናቸው ዝናብ መጠበቅ የህዝቡ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የሶማሊ ህዝብ በሀገሪቱ ስልጣን ላይ ከነበሩት የቀድሞ ንግስት ነጋስትና አንባገነኑ ወታደራዊ መንግስታት አይደለም መስረተ ልማትና ምንም አይነት ጥቅም ሳያገኝ የቆየ ማህበረሰብ ቢሆንም፡ ባሳለፍናቸው 10 አመታት የክልሉ የገጠሩ አርብቶ አደርና ከፊል አርአደሩ ማህበረሰብና እንደሁም የከተሞች ነዋሪዎች የውሃ ፍላጎትና ጥያቄ በኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ እና በአቶ አብድ መሀሙድ ኡመር መንግስት በተሰጠው እሊህ አስጨራሽ የወሃ ዝርግታና ፈጣን ምላሽ የክልሉ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር እንድረጋጋና በውሃ፡በሳርና በግጦሽ ፈለጋ ከቦታ ወደ ቦታ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ማህበረሰብ ሁሉም ባሉበት አከባቢ በቋሚነት እንድረጋጉ አደርጓል፡፡
ዱሮ ግን ከክልሉ ዋና ከተማ ከጅግጅጋ በሁሉም ሲትጓዝ በቅርቡ ውሃን የሚተታገኘው ቢያንሲ ከ180ኪሜ ተቋርጠህ በደጋህቡር በዋርዴር ቀ/ደሀር ወይም በድሬደዋ መሀከል ምንም አይነት ውሃ የሚባል ነገር እንዳል ነበረ ይታወቃል፡፡
በዚህ መሰረት በኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓርት የሚመራውን የክልሉ መንግስት ልዩ ስተራቴጂ በመንደፍ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ከ1ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ ከመሆኑ ባሻገር ለሌሎች የኢትዮጲያ ክልሎች ተምሳሌት በመሆኑ ከማንም ያልተሰወረ ጉዳይ ነው፡፡
በሌላ በኩል የክልሉ ውሃ ሀብት ቢሮና የውሃ ስራዎች ግንባታ ድርጅት ከክልሉ ዲዛይንና ቁጥጥር ኢንተርፐራይዝ ጋር በመተባበር በርካታ የውሃ አከባቢዎችን በማጥናት የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ የውሃ ማጣሪያ ማሽኖች ከውጭ በማስገባት የዝናብ ውሃ ማቆሪያ ግድቦች በተለያዩ ወረዳዎችና ቀበልዎች በመገንባትና በወንዞች አከባቢ የሚኖሩ ማህበረሰብ የተፋሰስ ውሃና መስኖ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉ የማይረሳ ታሪካዊ አሻራ ሆኗል፡፡
በዚህ ረገድ የክልሉ መንግስትም ከ1200 ሜትር በላይ ጥልቀት የከርስ ምድር ውሃ ማውጣት የሚችሉ፡ ጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች መቆፈሪያ ማሽኖችን ከውጭ በመግዛትና አገልግሎት ላይ በማዋል አመርቂ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ችሏል፡፡
በሌላ በኩል የኢትዮጲያ ሶማሊ ክልል መንግስት በዞንና በወረዳ ደረጃ 180 መካከለኛ የውሃ ማቆሪያ ግድቦች ግንባታ የተከናወነ ሲሆን ግድቦቹ 873,019 851 ሜትር ኪዮቢክ ውሃ መያዝና የማጠራቀም አቅም ያላቸው ናቸው፡፡
በተመሳሳይም መሆኑም ከዛሬ 10 አመታት በፊት የነበረው የውሀ ቢርካዎች ቁጥር ከ320 ወደ 3900 ለማሳደግ ተችሏል፡፡ በዚህ መሰረት በኢትዮጲያ ሶማሊ ክልል አከባቢ የተለያዩ የአገራችን የግልና የመንግሰት ሚዲያ ባላሙያዎች እንደ EBC ሶማለኛና አማረኛ ፖሮግራሞች ዋልታ ፡EBSTV፡ ኢትዮጲያ ፐሬስ አጄንሲ፡ ኢ.ዜ.አ፡ ዛሚ ኤፍ ኤም፡ESTVና የመሳሰሉት ሚዲያዎች በክልሉ እየተከናወኑ ላሉ ዘርፈ ብዙ ልማትን በተለያዩ ወረዳዎች በተዘዋወሩና በተላይ ውሃን አስመልኪቶ በጎበኙበት ወቅት በፋፈን በቸረርና ቆረሄይ ዞኖች ላይ የተሰሩ የዘላቂ ልማት ሜጋ ፖሮጀክቶች እንደ በካ- ቢርቆት:የሻይኮሽ ጎማር ወቺዋችና እንድሁም የመረኣቶ የመስኖ ሀፈር ዳሞች ለክልሉ ህዝብ ውሃና ገብሪና ፈላጎት ዘላቂ መፍትሄ መሆናቸው አስመስክሯል፡፡እንደዚሁም የውሃ ቢርካዎችሁ የክልሉ ህብረተሰብ የውሃ ፍላጎት ለመሸፈን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ መሆናቸውም አስረድቷል፡፡
በተመሳሳይም በፋፋን እና ጀረር ወንዞች በከረምት ወቅት የሚፈሰውን የጎርፍ ውሃ 18ሺ ሄክታር መሬት ላይ ለማልማት በመሮዓቶ፣ በካ ፣ቢርቆት፣ጎማርና ወቺዋች የተገነቡ ዘመናዊ የመስኖ ፕሮጅክቶች ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ በአከባቢው ህዝቢና መንግስት እታረሱ ሲሆን እነዚህ ፕሮጅክቶች በቅርቡ በ100 ሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከውሃ አልፎ በምግብ ዋስትናና ሰብል ራሳቸውን እንዲችሉና ተጠቃሚ እንድሆኑ ያደርጋሉ፡፡በሌላ በኩል ከላይ የተጠቀሱት ወረዳዎች ውስ፡በመጨረሻውን ዓመታት የነበረባቸው የውሃ ችግር ከተቃለለላቸው አከባቢዎች መካከል አራርሶ፣ በለፋእሳ፣ደኖት፡ገላዲ ሐሮራይስ፣ መጋለአድ፣ ዱማሌ ፣ ዱዱሞአድ፣ ጎግቲ ላሰአኖድ ፡ ሌሄለው፡ ቦህ፡ጉናገዶ፡ቱሉጉሌድ፣ ጌድሉጋስ (ሚኤይስ)ሽላቦ አዋሬና አሌን ተጠቃሽ ናቸው፡፡በተመሳሳይም በካሃ ቀ/በየህ ሀርተሼክ ዱርዋሌ የውሃ ዝርጋታ ፖሮጀክትና ሙግወይን ፊቅ ሀመሮ ገሳንገስና የገሊል ኦበሌ ጌዲ ህግለሌይ ደ/ቡር የሰውና የእንስሳት ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፖሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ የአከባቢው ህዝብ ተጠቃሚ አደርጓል::
በመቀጠልም በፋፈን፡ቸረር፡ቆረሔይና በዶሎ ዞኖች ላይ ከአሁን በፊት በርካታ የውጭና በአገር አቃፍ ድርጅቶች ተጠንቶ ውሃ የለም የተባሉት አከባቢዎች በክልሉ አቅም ተጠንቶ በተላይ በለሄለው፡በዋርዴር፡በደኖት፡መርሲን ጉናገዶ ዲግ፡ሀርሽን፡ ጋሻሞ ወረዳዎች ላይ ከቢርቆት ተነስቶ 170ኪ.ሜ በማቋረጥ በቀይ አፈር ላይ የተቆፈሩ የሰውና የእንስሳት ንፁህ የመጠጥ ውሃ ጉድጓዶች ለህዘቡ ምላሽ ከመሆናቸው ባሻገር እንደ “ፓትሮሊየም” መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ እንዴ የክልሉ ውሃ ሀብት ቢሮ ሪፖርት የክልሉ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለሁት ሲንካፈል፡ የከተሞች ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን ከአቶ አብድ መሀሙድ ኡመር መንግስት በፊት በአማካኝ 10 በመቶ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 70 በመቶ ደርሷል ፡፡የክልሉ ከተማ መስተዳደሮች እየአንዳንዱ 5ኪሜ የዉሃ ጣቢያዎች ተተኬሎ እየሰራህ ይገኛል፡፡
የገጠር ንጹህ የመጠጥ ውሃ ሽፋን ከጥቅት አመታት በፊት 8 በመቶ የነበሬ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ወደ 59 በመቶ ሽፋን እንዲያደግ ተደርጓል፡፡
የክልሉ መንግስት በአጠቃላይ በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት በማጥናትና ከሁሉም ዘርፍ የተለየ ትኩረት በመስጠት በገጠርና በከተሞች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ስራ በጥቅሉ ከ10 አመት በፊት 278የነበሩ ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶችን ወደ 670ለማሳደግ ችሏል፡፡ የእጅ ውሃ ጉድጓዶች ከከጥቅት (10) አመታት በፊት 320 የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 2, 934 መድረሱ የማይካድ ሀቅ ነው፡፡
ዘጋቢ:- አብዱረዛቅ ካፊ