ጅግጅጋ (Cakaaranews) እሁድ፤ግንቦት 26/2010ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አከባቢ ጥበቃ᎓ማዕደን᎓አኔርጂና ደን ልማት ኤጄንሲ ሰረተኞች ከጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር አመራር አካላትና ሰረተኞች ጋር በመተባበር በክልሉ መንግስትርዕሰ መዲና በሆነችው በጅግጅጋ የአለምአቀፍ የአከባቢጥበቃ ቀንን ምክንያት በማድረግ በከተማው የፅዳት ዘመቻ ስራ አከናወነዋል፡፡ የፅዳት ዘመቻው በዋነኝነት ጅግጅጋ ከተማንፅዱናአረንጓዴለማድረግእንዲሁምአካባቢንማፅዳትየኅብረተሰቡቋሚተግባር ከማድረግ ጋር የተያያዘ ስራ መሆኑንም ተገልጸዋል፡፡
በዚህም የፅዳት ዘመቻው ዋና አለማ ጅግጅጋ ከተማንፅዱናአረንጓዴለማድረግ፣ በከተማው ህብረተሰብ ላይ የሚታየውንየቆሻሻአያያዝጉድለትለመቅረፍ እንዲሁም በቆሻሻምክንያትየሚከሰተውብክለትለአካባቢደህንነትአንዱናዋነኛውአሳሳቢጉዳይመሆኑንና የአከባቢጥበቃናአረንጓዴልማትሥራዎችወሳኝ መሆኑን የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አከባቢ ጥበቃ᎓ማዕደን᎓አኔርጂና ደን ልማት ኤጄንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መውሊድ ሃይር ሀሰን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ዋና ሥራ አስኪያጅጁ በክልል ደረጃ በካራመርዳ ተራራ የተከናወነው የአከባቢ ጥበቃና የፅዳት ቅስቀሳ በአለምአቀፍ የአከባቢጥበቃ ቀንን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ መርሀ-ግብር መሆኑንም አብራርቷል፡፡
በሌላ በኩል የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዲአዚዝ መሀድ ዝግጅቱ ጅግጅጋ ከተማንፅዱናአረንጓዴለማድረግ እንዲሁም ሶዎች በከተማው ውስጥ የሚጣሉት ደረቅ ቁሻሻዎችን ለማስወገድ የታለመ የፅዳት ስራ ነው ብሏል፡፡በአጠቃለይ በከተማው እየተከናወነ ያለው የፅዳት ቅስቀሳ ተግባራት “ደረቅ ቁሻሻዎችን እንዋጋለን” የሚል መሪ ቃል ተከብረዋል፡፡