ጅግጅጋ (Cakaaranews) አርብ፤ግንቦት24/2010 ዓ.ም.በዛሬው እለት በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በሚገኙ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች የ10ኛክፍልብሔራዊፈተና በሰላምና ጥሩ ሁኔታ መጠናቀቁን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራህም አደን መሀድ ገልፀዋል። የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ደግሞ ግንቦት 27/2010 ዓ.ም እንደጀምርና በግንቦት 30/2010ዓ.ም ከ3 ቀናት በኋላ ይጠናቃል ብሏል ቢሮ ኃላፊው።
በክልሉ የ12ኛ ክፍል የዩኔቬርሲቲ መግቢያ ፈተና ለሚፈተኑ የተማሪዎች ብዛትም 10,008 ተማሪዎች ሲሆን ፈተናው የሚሰጥበት የክልሉ 98 ት/ቤቶችም ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውም ገልጿል።
የ10ኛና የ12ኛ ክፍል ፈተናዎች መጠናቀቅን ተከትሎ የ8ኛ ክፍል ሚንትሪ ፈተናም ከሰኔ 11 እስከ 13/2010ዓ.ም. በክልሉ 547 ት/ቤቶች እንደሚሰጥም የት/ቢሮ ኃላፊው አስረድቷል ። ለ8ተኛ ክፍል ሚንትሪ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች ብዛትም 33,713 መሆኑንም አስታውቋል።