ቀብሪበየህ(cakaaranews)ሀሙስ፤ግንቦት 23/2010. የዘንድሮ ሀገር አቀፍ ፈተና በተመለከተ የቀብሪበየህ ከተማ ትምህርትና አቅም ግንባታ ጽ/ቤት በተለይም ከተማሪዎች ከወላጆች፤ከመምህራንና በአጠቃላይ በየደረጃው ከሚገኙ አካላት ጋር ጥልቅ ውይይቶችን በማድረግ በተግባርና በስነ-ልቦና ዝግጅቶች መደረጉንም የትምህርት ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ረቢዕ መዓሊን መሀመድ አስታውቋል።
በከተሟ የብሔራዊ ፈተና በሚሰጥበት የዶ/ር አብዱል መጂድ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ፈተናው በጊዜው የገባ መሆኑን የገለጹት የከተማው ትምህርትና አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ የቀብርበየህ ከተማ አስተዳደር የዶ/ር አብደልመጂድ ሁሴን 2ተኛና መሰናዶ ት/ቤት ባለፈው አመት የ10ኛ ክፍል ፈተና ተማሪዎች ውጤት መልካም እንደነበረም የገለጹት ሲሆን “ባለፈው አመት በዚህ ት/ቤት ብሔራዊ ፈተና የተፈተኑት ተማሪዎች ጥሩ ውጤት አስመስግበዋል፤የዘንድሮም ከበፊቱ የተሻሌ ውጤት እንደሚያመጡም ሙሉ እምነት አለን” ብሏል የት/ት ፅ/ቤቱ ኃላፊ።
የ2010የሃገር አቀፍ ፈተና ጥሩ ውጤት ለማስመስገብም የከተማ አስተዳደሩ ትምህርትና አቅም ግንባታ ጽ/ቤት የተለየ ዝግጅት መደረጉ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ረገድ 267 ወንድና 109 ሴት ተማሪዎች የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እየወሰዱ ከመሆኑ ባሻገር “የቀብሪበየህ ከተማ አስተዳደር ት/ት ፅ/ቤት ከከተማ አስተዳደር አመራርና ከተማሪዎች ወላጅ ጋር በመተባበር ለ10ኛ ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ተማሪዎችን የከበዳቸው የትምህርት አይነቶች በቅድመ ዳሰሳ በመለየት የማጠናከሪያ ትምህርትና ተጨማሪ ግንዛቤ እንድሰጥ አደርገናል” ሲሉ ገልጿል።
በሌላ በኩል የቀብሪበያህ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙክታር መሀመድ አብዲ በ2010 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና በሚፈተንበት የዶ/ር አብዱል መጂድ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት በመዘዋወር በፈተና ላይ ያሉት ተማሪዎችን ሁኔታ ጎብኝቷል።
በተጨማሪም የቀብሪበየህ ከተማ 2ተኛና መሰናዶ ት/ቤት ከ10ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በተጨማሪ የዩኒቬርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀም የከተማ መስተዳድሩ ትምህትና አቅም ግንባታ ፅ/ቤት አስገንዝበዋል።