Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የጤና ሽፋን 62 በመቶ መድረሱን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ

$
0
0

ጅግጀጋ(Cakaarnews) ሐሙስ ፤ ግንቦት 23/2010 ዓ.ም በኢ.ሶ.ክ የእናቶችና ህፃናት ሞት በሚታይ መልኩ በጉልህ መቀነስ የቻለ ሲሆን ቀድሞ ከ1ሺህ ወላድ እናቶች ውስጥ 871 የሚሆኑት በሞት አደጋ ውስጥ ነበሩ። ዛሬ ላይ ይህ ቁጥር በእጥፍ ቀንሷል። የክትባትና ሌሎች ግልጋሎቶችም እንዲሁ የማህበረሠቡን የአኗኗር ዘይቤ በተከተለ መልኩ እየተሰጠ መሆኑን ተገለጸ። ዛሬም በክልሉ የኒሞኒያ እና የተቅማጥ በሽታዎች ከሌሎች ይልቅ ጡንቻቸው የበረታ ሲሆን እነሱና ሌሎች በሽታዎችን የመከላከሉን ሥራ ተደራሽ ለማድረግም እየተሠራ ነው ተብሏል።

በተያያዜም የተለያዩ አጋር ድርጅቶችም በእነዚህና በሌሎች የጤና ሽፋኑን ማሻሻል በሚቻልባቸው ዘርፎች ላይ በትኩረት እንዲሠራ ስምምነት ላይ ስለመድረሡ የጤና ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ አይደሩስ አህመድ ተናግረዋል። በኤሌክትሪክ እና በውሃ መሠረተ ልማቶችን ማሟላት የሚለው እንዲሁ በጤና ተቋማቱም  የትኩረት መስክ መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋለ። የጤና ባለሙያዎች ቁጥርን ለመጨመርም በርካታ አመርቂ ሥራዎች ተከናውነዋል ብሏል። በዚህ መሠረትም ቀድሞ በክልሉ አንድ ዶክተር በአማካኝ ለ78 ሺህ ታካሚዎች ያገለግል የነበረ ሲሆን አንድ ነርስ ደግሞ ለ12 ሺህ ተካሚዎች ታገለግል ነበር። አንድ አዋላጅም እስከ 20 ሺህ ለሚጠጉ ወላድ እናቶች የማገልገል ሃላፊነት ነበረባት። ዛሬ ላይ ግን አንድ ዶክተር በአማካኝ ለ31 ሺህ ታካሚዎች፣ 1 ነርስ ለ1,800 ታካሚዎች እንዲሁም 1 አዋላጅ ለ8 ሺህ ወላድ እናቶች እንደሚያገለገሉ ም/ኃላፊው አብራርቷል።

ከ10 ዓመታት በፊት የነበረው የጤና ሽፋን 7 በመቶ እንደነበር በማስታወስ ዛሬ ላይ ግን ወደ 62 በመቶ ከፍ ስለመደረጉ ነው የጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊው አቶ አይደሩስ አህመድ የተናገሩት። እንደ ኢትዮጵያ ሶማሊ ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ ገለፃም ከሆነ የጤና ሽፋኑን ለማሳደግ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ክልል ድረስ የአመራር  ቁርጠኝነቱን በማረጋገጥ ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ የተለያዩ ሥራዎች ተከናውነዋል። በዚህም መሠረት ቀድሞ 3 አጠቃላይ ሆስፒታሎች፣ 20 ጤና ጣቢያዎችና 80 ጤና ኬላዎች የነበሩት ሲሆን አጠቃላይ የነበረው የጤና ባለሞያዎች ቁጥርም ከ1,700 አይበልጥም ነበር ብሏል።

በየደረጃው የተከናወኑ ጥረቶችም የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችለው የአጠቃላይ ሆስፒታሎች ቁጥር ወደ 12 ከፍ ያለ ሲሆን 260 ጤና ጣቢያዎች እና ከ1500 በላይ ጤና ኬላዎች ለማህበረሠቡ ግልጋሎት እንዲሰጡ ማድረግ ተችሏል ብለዋል ም/ቢሮ ሃላፊው አቶ አይድሩስ አህመድ።በተጨማሪም ከተለያዩ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋርም በጋራ በመሆን 28 ተንቀሳቃሽ የህክምና ቡድን በሥራ ላይ ሲሆን በክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ጠንሳሽነት በሥራ ላይ የሚገኘው ተንቀሳቃሽ የዓይን ህክምና ቡድንም ለጤና ሽፋኑ ማደግ የራሳቸው ጉልህ አስተዋፅኦ ስለመሆኑ አስረድቷል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>