Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መውሰድ ተጀምሯል

$
0
0

ጅግጅጋ (Cakaaranews) እሮብ፤ግንቦት 22/2010..በዛሬው እለት በአጠቃላይ በኢ.ሶ.ክ በክልሉ በሚገኙ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች 10ክፍልብሔራዊፈተና መስጠት ተጀምሯል። በፈተና አሰጣጡ ሂደት ላይ የኢ.ሶ.ክ.መ ት/ቢሮ ሃላፊ ፣ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ፣ የክልሉ ት/ቢሮ የፈተና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና ሌሎችም የክልሉ መንግስት ሃላፊዎች በጅግጅጋ ከተማ የሚገኙትን የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በመጎብኘት እና እንዲሁም በቦታው በመገኘት የፈተና አሰጣጥ ስነ-ሥርዓቱን ተከታትለዋል፡፡

በመሆኑም በመላው የኢ.ሶ.ክ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች ፈተናው በዛሬው እለት በይፋ እንደተጀመረ ፣ በክልሉ 10ክፍልብሔራዊፈተና  የሚወስዱ ተማሪዎች ቁጥር 19,450 እንደሆነና በክልሉ ባሚገኙት 11 ዞኖች፣ 93 ወረዳዎች እና 6 የከተማ መስተዳድሮች በአጠቃለይ በ165 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ፈተናው በጥሩ ሁኔታ እየተሰጠ መሆኑን የኢ.ሶ.ክ.መ  ት/ቢሮ ሃላፊ ክቡር አቶ ኢብራህም አደን መሀድ ገልፀዋል፡፡ በአጠቃላይ በክልሉ 527 ፈታኞች እና 124 የፈተና ሂደት ክትትል ቡድኖች (ሱፐርቫይዘሮች) የተመደቡ መሆኑንና የፈተና ሂደቱንም የሚከታተሉ መሆኑን አያይዞም ቢሮ ሃላፊው ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የክልሉ ት/ቢሮ ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር በቅርብ ዓመታት በክልሉ ያለዉን የትምህርት  ተደራሽነት እና ጥራት ከፍ በማድረግ እንዲሁም ከ7000 በላይ ተማሪዎች ማለትም 71በመቶ የሚደርሱ የክልሉ ተማሪዎች በብሔራዊ ፈተናው ውጤት የተሳካለቸው እንደነበረ በምሳሌነት በማንሳት ቢሮ ሃላፊው  አክለው ተናግረዋል፡፡      

በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት በትምህርት ዘርፍ  የተፈለገውን  የተማረ የሰው ኀይል በማፍራት ሰፊ ሥራዎችን በመስራት እንዲሁም ለክልሉ ማህበረሰብ የትምህርት ሽፋንን ተደራሽ በማድረግ፣ የተፈለገው ደረጃ እና ዉጤት እንዲሁም ጥራት ባለው መልኩ ባሉበት አካባቢ በማዳረስ ላይ ይገኛል፡፡ በአጠቃለይ 10ክፍልብሔራዊፈተናውም በአጠቃላይ እንደ ሃገሪቱ በክልሉም ለሚቀጥሉት ሶስት ተከታተይ ቀናት ቀጥሎ እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>