ጅግጅጋ(cakaaranews)ሰኞ፤ግንቦት 20/2010ዓ.ም.27ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል ለላቀ ብሔራዊ መግባባት እና የዴሞክራሲያዊ አንድነት ለላቀ ሃገራዊ ስኬት በሚል መሪ ቃል በመላው ሃገሪቱ የተከበረ ሲሆን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መዲና በጅግጅጋ ከተማ በሰይድ መሀመድ አብዱሌ መሰብሰቢያ አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ ተከብረዋል። በክብረ በዓሉ ላይ የኢ.ሶ.ክ.መ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር የተገኙ ሲሆን የክልሉ መንግስትና የክልሉ መሪ ፓርቲ ኢሶህዴፓ ከፍተኛ አመራር አባላት፤የክልሉ ሴክተር መ/ቤቶች ቢሮ ኃላፊዎች ፣ የሃገር መከላከያ ሠራዊት፤የክልሉ የፖሊስ ሠራዊት አባላትና አመራር ፣ ሃገር ሽማግሌዎች፤የእምነት አባቶች፤ሴቶች፤ወጣቶችና የከተማው ነዋሪዎችም ተካፋይ ሆነዋል።
ይህ ለ27ኛ ጊዜ ተከበረው የግንቦት 20 የድል በዓል የኢትዮጵያ ብሔር፤ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባለፉት ሥርዓቶች መብታቸው ተነፍጎ ማንነታቸው ተሽሮ በጭቆና ስር ይዟቸው የነበረውን አገዛዝ በመቃወም ሥርዓቱን የገረሰሱበትና ለዛሬ ማንነታቸው ዋስትና ያረጋገጡበት የዴሞክራሲ ሥርዓት የዘረጉበት የሠላም፤፤የነጻነትና የልማት ዕለት በመሆን በመላው የሃገሪቱ ክፍሎች እየተከበረ ይገኛል። ታዲያ በጅግጅጋ ሰይድ መሀመድ አዳራሽ በተከበረው 27ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል በመጀመሪያ ንግግር ያደረጉት የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር በአዳራሹ ለተገኙት የበዓሉ ታዳሚዎች እንኳን አደረሳችሁ ካሉ በኋላ ግንቦት 20 ለኢትዮጵያዊያን ብሔር ፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የነጻነት እና የማንነታቸው ማረጋገጫ ዋስትና ቀን እንደሆነ ገልጸው ግንቦት 20 ማለት ለኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብም ሠላምና የልማት ዋስትና ማለት መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብም እንደሌሎች ወንድም ብሔሮች የራሱን መብትና ነጻነት አግኝቶ ዛሬ ያለበትን ሠላም ፣ ልማትና ብልጽግና የተጎናጸፈበት ቀን ነው ብሏል ፕሬዝዳንቱ።
በተጠማሪም ክቡር ፕሬዝዳንቱ የግንቦት 20 ፍሬዎች ሲያብራሩ “ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች በተለይ ለኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ እንኳን ለ27ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል በሠላም አደረሰን አደረሳችሁ እላቹዋለው፤ ግንቦት 20 ማለት ለኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ውሃ ማለት ነው ጤና ማለት ነው ብዬ ነው የማስቀምጠው ምክንያቱም ከግንቦት 20 በፈት በነበሩት ሥርዓቶች እንደ ደርግ ወይም ከዛ በፊት በነበረው የነገሥታቱ ሥርዓት የክልሉ ህዝብ እንደ 2ኛ ዜጋ የሚታይ የነበረ ህዝብ ነው ከግንቦት 20 ድል በኋላ በተፈጠረው እራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንደ ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች እኩል መብት ያገኘ ህዝብ ነው ስለዚህ ግንቦት 20 ሠላም ነው ብዬ ነው የሚወስደው ምክንያቱም የኢትዮሶማሌ ህዝቦች ዜግነቱ እንደ 2ኛ ዜጋ ተደርጎ ሲቆጠር የነበረ ክልል እና ህዝብ ነው። የኢ.ሶ.ክ ህዝብም ከግንቦት 20 ድል በኋላ ነው ልክ እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ ህዝቦች ኢትዮጵያዊነቱ የተረጋገጠው መብትም እንዲኖረው የተደረገው በዚህ ምክንያት ነው ግንቦት 20ን ከሌሎች ክልሎች በተለየ መልክ ልናየው የምንችለው ግንቦት 20ን በአጭሩ ለመግለጽ ሠላም ነው ለሶማሌ ክልል።”
ክቡር ፕሬዝዳንቱ አክለው ሲገልጹም “በአንድ ወቅት በክልሉ የነበረው የፀረ ሠላም ሃይሎች እንቅስቃሴ በዜጎች ላይ ሲያደርስ የነበረውን ጥፋት በወቅቱ የነበሩት አመራሮች ከፀረ ሠላም ሃይሎች ጋር የነበራቸው ቁርኝት እንደነበረና ያንንም የጥፋትና የጠባብነት አመለካከት አሁን ላይ ያሉት አመራሮች ከህዝቡ ጋር ባደረጉት ጠንካራ ትግል ዘላቂ ሠላምን ማረጋገጥ መቻሉን ጠቆሟል። አሁን ላይ የሚናደርገው ትግል ግን ድህነትን አጥፍተን ልማትና ብልፅግናን ማምጣት ላይ እንደሆነ ገልጿል።
ሌላው በክልል አካባቢዎች እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ከነበሩ የፀረ ሠላም ሃይሎች እንደ አሊተሃድ ፣ አልሸባብ እና ኡቦ(ኦብነግ) ጋር ሲያደርግ የነበረው እልህ አስጨራሽ ትግል የማይረሳ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም እንደሚታወቀው ክልሉ የሚገኝበት አካባቢ የሃገሪቱ ድንበር እንደመሆኑ የውጪ ሃይሎች ወደ ሃገሪቱ ሰርገው እንዳይገቡ ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመተባበር የራሱን ድርሻ ሲወጣ እንደነበረ መታወስ አለበት ሲሉ አብራርቷል።”
በተያያዜም የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አብዲ መሀሙድ የክልሉ ጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን እንደሚያሻሽሉና በክልሉ ርዕሰመዲና የሚገኘው የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ሪፊራል ሆስፒታል ከፍተኛ ልምድና እውቀት ያከበቱ ሃክሞች በወራት ውስጥ ከውጭ ሃገራት እንደሚያመጡ እንደሁም እንደነ ጀርመንና ታይላንድ ሀገራት ያሉ ሃገራት የሚጠቀሙ ዘመናዊና ጥራቱን የጠበቁ የጤና አገግሎች መሳሪዎችን የክልሉ መንግስት ከውጭ እንደሚያመጡ ከመግለጻቸው ባሻገር የወጣቶች ስራ አጠኔት ለመቀነስ ያህል በሁሉም የክልሉ ወረዳዎች ለሚገኙ ወጣቶች ለያንዳንዱ ወራዳ 300 ወጣቶችን እንደሚቀጠሩለትም አክሏል።
በሌላ በኩል በክብረ በዓሉ ታድመው ከነበሩት የሃገር መከላከያ ሠራዊት አመራር አባላትም ስለ ግንቦት 20 ሲገልጹ “ከዚህ የቀደመውን አጠቃላይ አስከፊ ሥርዓት ኢትዮጵያዊያን በጋራ በመታገል የገረሰሱበት ቀን በመሆኑ እንኳን ለ27ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል በሠላም አደረሰን በማለት ሲሆን ይህ እለት ከዚህ ቀድሞ የነበሩትንክፉ የአገዛዝ ሥርዓቶችን ለመገርሰስ ትልቅ መስዋዕትነት የተከፈለበት እንደሆነ ጠቅሰው ዛሬ የተገኘውን ሠላም ፣ አንድነት ፣ ልማትና ብልጽግና በጋራ አስጠብቆ መዝለቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።በተጨማሪም የመከላከያ ሠራዊት አመራር አባላትም በዚህ ቀን በተገኘው ሠላም አማካኝነት ሀገራችን የያዘችውን የዕድገት እና የህዳሴ ጉዞ ለማስቀጠል ቃል የምንገባበትና አንድነታችንን የምናረጋግጥበትና የሚናጠናከርበት እለት በመሆኑ ይህንንም ጉዞ ለዝህባችን እና ለሃገራችን እንደምናረጋግጥ ቃል እንገባለን ሲሉ አስገንዝበዋል”።