ጅግጅጋ(cakaaranews)እሁድ፤ግንቦት 12/2010ዓ.ም. በአውበሬ ወረዳ በተዘጋጀው 12ኛው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሠላም ፣ የልማት፤የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና የመልካም አስተዳደር የህዝብና መንግሥት የጋራ መድረክ ላይ የተገኙ የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራዎች በክልሉ እየታየ ባለው ዘርፈ ብዙ የልማት ዕድገት መደሰታቸውን የገለፁት ተሳታፊዎች የጋራ መድረኩ ሁሉን ያሳተፈ እንደነበርም ተናግረዋል።
በተጨማሪም በአውበሬ ከተማ በተዘጋጀው 12ኛው የኢ.ሶ.ክ ህዝብና መንግሥት የጋራ መድረክ ላይ የተገኙ የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራዎች ከሁሉም የክልሉ ዞኖች፤ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ የማህበረሰብ ክፈሎች ሃሳባቸውን ያለምንም ጫና በነፃነት በመለዋወጣቻው ከመጡባቸው አገራት ጋር ሲያነፃፅሩ የመድረኩ መሪ የነበሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አብዲ መሀሙድ ወንድ ፣ ሴት ፣ ትንሽና ትልቅ ወጣትና ሽማግሌ ሳይሉ ከሁሉም የሚሰነዘሩላቸውን ሃሳቦች በአንድነት ተቀብለው ምላሽ ሲሰጡ በማየታቸው በእጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
አያይዘውም ለዚህም ዋናው ምክንያት በክልሉ በተገኘው ሠላም ሲሆን ክልሉ ትላንት የት እንደነበር፣ ዛሬ ምን ላይ እንዳለና ነገን ደግሞ ምን ላይ ለመድረስ እንደምንፈልግ ከዚህ የጋራ ምክክር መድረክ ትልቅ ግንዛቤ እንደጨበጡ በመግለፅ ከአሁን በፊት በአደጉበት የክልሉ አካባቢዎች ስለነበረው የሠላምና የትምህርት መሠረተ ልማት ተደራሽነት እጦት ምክንያት ከተያዩ የሶማሌ ክልል ወረዳዎች የተሰባሰቡ ወጣቶች ጋር በመሆን በሐረር እንደተማሩ የዲያስፖራ አባላቱ ተናግረዋል። ነገር ግን ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ያሉት ወጣቶች ባሉበት አከባቢ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድረስ በክልሉ መንግስት በተመቻቸላቸው የትምህርት የትምህርት መሠረተ ልማት ተቋማት እንደሚማሩና በጣም ዕድለኞች እንደሆናቸውም ገልጸዋል።
በተያያዜም ከዚህ በተሻለ ሃገራችንም ክልላችንም ዕድገት እንዲያሳዩ እንፈልጋለን ምክንያቱም ከሌሎች ሠላማቸውን ካጡ ሃገራት ትምህርት መውሰድ መቻል አለብን ይህንንም ማስቀጠል የሁላችንም ድርሻ ከመሆኑ ባሻገር በሠላም የተረከብናትን ኢትዮጵያ እኛም በኩላችን በሰላም ፣ በፍቅርና በብልጽግና ለሚቀጥለው ትውልድ ማስረከብ ግዴታ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ማለት መፋቀር ማለት ነው። እኛን የኢትዮጵያ ሶማሌዎችን ከሌላው የሚለየን ችግር በሚገጥመን ጊዜ እንደሌሎቹ ሶማሌዎች ጎሳችንን አይደለም የምንለው እንጅ ሃገራችንን ነው የምንለው፤ ሃገራችን ማን ናት?ኢትዮጵያ ናት ደግሞም በኢትዮጵያዊነታችን እንኮራለን ሲሉ በጉባአው የተገኙት የዲያስፖራ አባላት ተናግረዋል።
የጋራ መድረኩ አጠቃላይ የክልሉን ነባራዊ ሁኔታን በመገምገም እና አበረታች ለውጥ የታየባቸውን ዘረፎች ለማስቀጠል ቃል የተገባበት ሲሆን የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ትናንት ከትናንት ወዲያ የሚታወቅበትን ሥም በመቀየር ዛሬ ላይ በክልሉ የሚታየውን የልማት ውጤቶችን ይበልጥ በማሳደግ ህዝብ እና መንግሥት በጋራ ሊሠራ እንደሚገባም ጉባኤው አቋም ወስዷል። 12ኛው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሠላም የልማት እና የመልካም አስተዳደር የህዝብ እና የመንግሥት የጋራ መድረክ ያስገኘው ውጤት ከፍተኛ እንደሆነም የተገለፀ ሲሆን ይህ ስብሰባ በዓመት ሁለት ጊዜ በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች እና ከተሞች ላይ እንደሚሰናዳም ይታወቃል።