Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት የመልሶ ማቋቋም ኮሚቴ አቋቋማል

$
0
0

አዲስአበባ(Cakaaranews)እሮብ፤ሚያዝያ 10/2010ዓም. የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ም/ቤት(ጨፌ)ከቀናት በፊት ያባካ መደበኛ ገባኤ የክልሉ ርዕሰመስተዳደር ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ለም/ቤቱ ያቀረቡት ሪፖርት ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ወገኖች መልሶ የሚያቋቋሙ ኮሚቴ ማቋቋሙን ገልጿል። የመልሶ ማቋቋም ኮሚቴ አባላቱ ከክልሉ ከፍተኛ አመራር አካላትና ከልሉ ም/ቤት አባላት የተወጣጡ ሲሆን በቅርቡ  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኙና በግጭቱ ሳቢያ ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተፈናቃዮችን ወደ ኦሮሚያ እንደሚወስዱም ይጠበቃል።

 ይህ ሰናይ እርምጃ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰመስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ስልጣና ጀግንነት በተሞላ በወወሰኑት ውሳኔ ተከትሎ የክልሉ መሪ ጅርጅትና መንግስት ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑን ያሳያል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ከአሁን በፊት እንዲህ ውሳኔዎች በማሳለፍና ተግባራዊ በማድረጉ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ በርካታ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ወደ ቀድሞ ቄያቸው ተመልሶ በአሁኑ ወቅት በአከባቢያቸው በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መደበኛ ስራቸው ተሰማርቶ በሰላም እየሰሩ ይገኛሉ።የኢትዮጵያ ክልል ሶማሌ መንግስት የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ብሎም የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ለማ መገርሳ መልካም ውሳኔን ደስተኛ መሆናቸው አስታውቀዋል።

 በመሆኑም በሞያሌ የተከሰተው ችግር የሁለቱም ብሔሮችና የሁለቱ ክልሎች የማይወከል አጸያፍ ድርግት መሆኑንና ከጥንት ጀምሮ ለዘመናት በሰላም አብሮ የኖሩ የኦሮሞና ሶማሌ ህዝቦች የቆየውን ባህልና እሴት ለማፍረፍ እንዲሁም በቅርቡ ከሁለቱ ክልል መሪዎች የተደረሰው የዘላቂ መፍትሄ ስምምነት እንዳይሳካ የፈለጉት ፅንፈኛና ጥቅመኛ ግለሰቦች ሴራ የተፈጸመ አስነዋሪ ተግባር መሆኑንም የኢትዮጵያ  ሶማሌ ክልል መንግስት አስታውቋል።

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>