Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ለኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ልዑኳን ቡዱን ደማቅ አቀባበልና ግብዣ አደርገዋል

$
0
0

ስቶክሆልም(cakaaranews)ማክሰኞ፤ ሚያዝያ 2፤2010ዓም. በኢፈዴሪ የስዊድን ባላሙሉስልጣን አምባሳደር ፖሮፌሰር መርጋ በቃና ፤በስቶክሆልም የኢትዮጵያ ቁንስላ ጽ/ቤት ሃላፊ አምባሳደር ሁሴን አህመድና ሌሎች የኤምበሲው አመራር አካላት በአውረፓ ሀገራት ለሚከበረው የኢሶህዴፓ 20ኛው አመት ምስረተበዓልን አስመልኪቶ ወደ ስዊድን  ያቀኑትና በኢ. ሶ.ክ.መ.ንግድ፤ ትራንስፖርትና እንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ፤ የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ከደር አብዲ ኢስማኢል የሚመራ የዲያስፖራ አባላትና የክልሉ መንግስት ጥምር ልዕኳን ቡዱን እንድሁም በስቶክሆልም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዲያስፖራ ኮሙኒቲ አመራር አባላት በስቶክሆልም ከተማ ደማቅ አቀባበል እና የእራት ግብዣ እንደተረገላቸውን በስቶክሆልም የኢትዮጵያ ቁንስላ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ምክክር መድረኩ ላይ መፍቻ ንግግር ያደረጉት የኢ. ሶ.ክ.መ.ንግድ፤ትራንስፖርትና እንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ከደር አብዲ ኢስማኢል በኢፈዴሪ የስዊድን ባላሙሉስልጣን አምባሳደር ፖሮፌሰር መርጋ በቃና እና በኢፈዴሪ የስቶክሆልም ቁንስላ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሁሴን መሀመድ እንድሁም ሌሎች የኤምቤሲው አመራር አካላት ለልዑኳን ቡዱኑ ባማረ መልኩ ባደረጉለት  ግብዣና ደማቅ አቀባበልን የላቀ ምስገና አቅርበዋል። በተያያዜም በኢፈዴሪ የስዊድን ኤምበሲና በኢፈዴሪ የስቶክሆልም ቁንስላ ፅ/ቤቱ በአጠቃላይ በስዊድን ሀገርና በስቶክሆልም ከተማ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዲያስፖራ ኮሙኒቲ አባላትና የክልሉ ተወላጆች በክልሉና ብሎም በሀገሪቱ እየተከናወነ ያሉት ዘርፈብዙ የልማት ስራዎች የበኩላቸው ድርሻ እንድወጡ በማነሳሳታቸውና የተለያዩ የምክር ድጋፍ በማድረጋቸው አበረታች ሥራ መሆኑን የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ከደር አብዲ አስረድቷል።

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>