Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

የአባቆረው ወረዳ አስተዳደር በወረዳው ለሚኖሩ ወጣቶች ሥራ ፈጠራ የሚውል የብር ድጋፍ ማመቻቸታቸው ተገለጸ

$
0
0

አባቆረው(cakaaranews)ማክሰኞ ሚያዚያ 2ቀን፣ 2010 ዓ.ም እንደሚታወቀው አገራችን ኢትዮጵያ ካሏት የተለያዩ ሃብቶች አንዱ የሰው ሀብት እንደሆነ የሚታወቅ ነው ፤ ከአገሪቱ ህዝብ አብዛኛው ደግሞ ወጣት እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ይህን የሰው ሀብት በአግባቡ በአገር ደረጃ በተቀረፁ የሙያ መስኮች በገበያ ፍላጎት መሰረት ወጣቶቹ በሙያ ሰልጥነውና ተደራጅተው በራሳቸው ስራ እንዲሰማሩ አገራችን የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅድ ካስቀመጠቻቸው ፖሊሲዎች አንዱ ነው ፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የክልሉን ወጣቶች የስርዓቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎችን እየተሰሩ ይገኛሉ ፡፡ ከ11 ዞኖች፣93 ወረዳዎቸ እና 6 የከተማ አስተዳደሮች የቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጆች በሚገባ ሁኔታ ተፈትነውና ሰልጥነው በተጨማሪም የምግብና የመኝታ አገልግሎት ጭምር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ወጣቶቹም በስልጠናቸው ብቁ ሆነው ከአጠናቀቁ በኋላ በየስራ መስኩ እንዲሰማሩ ተደራጅተው ፤የብድር ድጋፍ ተደርጎላቸው በቀጥታ ወደ ሥራ እንዲገቡ እንዲሁም ክትትልና ድጋፍ እንዲደረግላቸው ሆኗል፡፡

በዚህ መሰረት በ2010 የበጀት ዓመት የአበቆረው ወረዳ  ለወጣቶች የሥራ ፈጠራ በተያዘው  በጀት ወረዳው ዉስጥ የሚገኙ ወጣቶችን የገበያ ፍላጎት ባላቸው ሙያዎች ሰልጥነው የብድር ድጋፍ በማድረግም ጭምር ወደ ሥራ እንደገቡ ተገልጿል፡፡ 381 የሚሆኑ ወጣቶችን በወረዳ ደረጃ  የገበያ ፍላጎት ባላቸው የሙያ መስኮች ስልጠና እንዲወስዱ በማድረግ ፤ ስልጠናቸውን አጠናቀው የሙያ ብቃታቸው ከተረጋገጠ  በኋላ በጥ/አነስተኛ ማህበራት ተደራጅተው  ወደ ስራ እንደተሰማሩ የወረዳው አስተዳዳሪ አስታውቋል፡፡ የሸቤሌ ዞን አመራሮች እና የአባቆረው ወረዳ አስተዳደር ሀላፊ በተገኙበት መድረክ ለወጣቶቹ የብድር ድጋፍ ስነስርዓት ተደርጎላቸዋል፡፡በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የሸቤሌ ዞን ም/አስተዳደር አቶ ኑር ሀይር ቃሲም ወጣቶቹን ያለባቸውን ክልላዊ ብሎም ሃገራዊ ሃላፊነት እንዲወጡ በመምክር መልዕክታቸውን አስተላልፈውላቸዋል፡፡ አቶ ኑር እንደተናገሩት አገራችን ትልቅ ተስፋ የጣለችበት ተቀዳሚ ሀብት በሆኑት በእኒህ ታዳጊ ወጣቶች እንደ ሃገር ያስቀመጠችው የእድገት ደረጃ የተፈለገውን ጊዜና ወቅት ጠብቆ ለማሳከት፤ ብሎም የወጣቱ ተሳትፎ ወሳኝ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የክልላችን መንግስት ለወጣቶች ምን ያህል ትኩረት መስጠቱን በተግባር የሚያሳይ ነው፡፡ እናንተ የዛሬ እድል ተጠቃሚ ወጣቶች የክልላችሁን ብሎም የመንግስታችሁን ህልም ለማሳካት ትልቅ የቤት ስራ ይጠብቃችኋል በማለት ነው፡፡

ተያይዞም የብድር ድጋፍ የተደረገላቸው የወረዳው ወጣቶች የተሰማቸውን ደስታ ሲገልፁ የበኩላቸውን ሃላፊነት እንደሚወጡ በመግለፅም ጭምር ነው፡፡ ዛሬ ያገኘነው እድል ከኛ በፊት የነበሩ ወጣቶች ያላገኙት ሲሆን እድለኞች ነን፤ ከአሁን በኋላ እረፍት የለንም የበኩላችንን ለመሥራትም የመንግሥታችንንም ህልም ለማሳካት ቀንና ለሊት እንሰራለን እናም እራሳችን ለዉጠን ህዝባችን ከደህነት ለማውጣት እንታጋለን በማለት ገልፀዋል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>