Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

በጀረር ዞን አስተዳደር ከደጋህመደው ወረዳ ሠራተኞች ጋር ውይይት ማካሄዱ ተገለፀ

$
0
0

ደጋህመደው(Cakaaranews)እሁድ፤ሰኔ 10/2010ዓ.ም . በጀረር ዞን የደጋህአመዶ ወረዳ በወረዳው ከሚገኙ አጠቃላይ የመንግስት ቢሮ ሠራተኞች ጋር የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱ ተገለፀ።  የውይይቱ ዋና ትኩረትም የ2010 ዓ.ም ማጠናቀቂያ እንደመሆኑና በቀጣዩ 2011 ዓ.ም በሥራና ሠራተኛው ሊኖር ስለሚገባው ጠንካራ የሥራ መንፈስን ተላብሶ የማስፈፀም ብቃትን ማዳበር በሚያስችልበት ጉዳይ ላይ መሆኑ ተገልጸዋል።

 በውይይት መድረኩ ላይ የወዳውን ለቀመንበር ጨምሮ የወረዳው ሠራተኞችም ተካፋይ ሆነዋል። የውይይቱ ዋና አላማ የ2010 ዓ.ም የሥራ ማጠናቀቂያ በመሆኑ ሠራተኛውና መስሪያቤቶቻቸው አፈፃፀም ምን ይመስል ነበር የሚለውን በማየት በቀጣይ 2011 ዓ.ም በወረዳው ልማት፤ ሠላምና መልካም አስተዳደር የሚኖረውን አፈጻፀምና ተግባራት በተሻለ ሁኔታ ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች መሆኑ የጀረር ዞን አስተዳደሪ ገልጿል።

የጀረር ዞን አስተዳደሪ አቶ ሙሁመድ ሀሰን ስለውይይቱን አላማ ማብራሪያ ሲሰጡ "ዛሬ የምንወያየው ስንከውናቸው የነበሩ ሥራዎች ምን ይመስሉ እንደነበር እንመለከታለን በተለይ በልማት፣ በሠላም እና መልካም አስተዳደር ላይ ከመጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን የነበረው አካሄድ ጥሩ ነበር አሁንም በዚሁ መልኩ እንዴት ማስቀጠል እንደምንችል የተሻለ ግንዛቤዎችን የምንወስድበት ይሆናል። ሌላው ሁላችንም በየመሥሪያ ቤቶቻችን የተሰጡን ሥራዎች ህዝብን የማገልገል ስሜት መጠናከር፣ የሥራ ሞራልና የተነሳሽነት ስሜቶችን ሠራተኛው በግልፅ ሊላበስና ሊያዳብራቸው ይገባል። የሥራ ሃላፊነት ደረጃው ይለያይ እንጂ ሁላችንም ሃለፊነት አለብን ስለዚህ ሥራን በተሻለና በተቀላጠፈ መልኩ መከወን አስፈላጊ ነው" ብሏል።

በተመሳሳይም በውይይቱ ላይ የማጠናከሪያ ንግግር የደረጉት የደጋህአመደው ወረዳ ሃላፊም "የ2010 ዓ.ም የሥራ ዘመን ተጠናቆ ወደ 2011ዓ.ምየሥራ ዘመን እየገባን በመሆኑ ለቀጣዩ ዓመት የታቀዱ እቅዶቻችን የወረዳው ሠራተኞች በጥልቀት እንዲረዱት እነሱም ድህነትን የማጥፋት ትግሉን በቀጠል ሃገራችን የያዘችውን የፈጣን ዕድገት ስትራቴጂና መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ የመሰለፍ ራዕይን ለማሳካት የሠራተኛው ጥረትና ተነሳሽነት ከበፊቱ የበለጠ መሆን ይገባዋል" ሲሉ ተናግሯል።

በመጨረሻም በውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ትልቁን ሚና የሚጫወተው ሠራተኛው በመሆኑ የበለጠ ተነሳሽነትን እንደየሥራ ድርሻቸው እንደሚተገብሩና ለልማት፣ ሠላምና መልካም አሰተዳደር መሳካት የበኩላቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>