Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከተለያዩ ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ መስተዳደሮች ለተወጣጡ 25ሺህ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አነጋገሩ

$
0
0

አዲስአበባ(cakaaranews)እሁድ፤ሚያዝያ 7/2010ዓም.የኢፌደሪ መንግስት የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ላይ እንደምትገኝ ከማንም ያልተሰወረ ትክክለኛ ጉዳይ ነው።በዚህም ከተለያዩ ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች ለተወጣጡ 25ሺህ የሚሆኑ የብሔር፤ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች፤የኢፌደሪ መንግስት ከፍተኛ አመራር አካላት፤የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድን ጨምሮ የዘጠኙ ክልሎች ርዕሳንመስተዳደሮችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ካንትባዎች በተገኙበት፤ህዝብና መንግስት የሚወያዩበትና የሚቀራረቡበት ምክክር መድረክ በኢስአበባ ከተማ  በሚሊንያም አደራሽ አካሄደዋል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሀገሪቱ የልማት ጀርባ አጥንት የሆኑት ወጣቶች በርካታ የልማት ስራዎች ተጠቃሚ እንደሚያደርጉና መንግስት ለወጣቶች በርካታ ስራዎች እንደሚያመቸቻችና እንደሚያሰማራም ተናግሯል።አያይዞም ወጣቶች አቅማቸውና እውቀታቸው ለልማትና ለመልካም ነገሮች እንድጠቀሙና መንግስት ሀገሪቱን ከሆላቀርነትና ደህነት የሚታወጣበት የልማት ህዳሴ ጉዞኦን የበኩላቸው ድርሻ እንደወጡ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አብይ አህመድ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠርና ሀገራዊ ጉዳዮች ለማጠናከር፤በሀገሪቷ ዴሞክራሲ ሥርዓት  ብሔራዊ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በማሳተፍና ሀገራዊ ጉዳዮችን ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በመናጋገር፤በመወያየትና መግባባት መንግስት በቅርበት እንደሚሰራም ገልጿል።ይህ መድረክ ታሪካዊ ምክክር መድረክ ከመሆኑ ባሻገር የኢፌደሪ መንግስትና የኢትዮጵያ ብሔር፤ብሔረሰቦችና ህዝቦች በፍቅርና በአንድነት በጋራ ሀገራዊ አንድነት ለማጠናከርና የጋራ ሀገራችን ዴሞክራሲ፤ሰላምና መልካም አስተዳደርን በጋራ የሚንሰራበት መድረክ እንደሆነም ዶ/ር አብይ አስረድቷል።መድረኩ የህዝቦች ጥያቄዎች በአግባቡ የሚመለስና ከህዝቡ ጋር በቅርበት የሚሰራ መንግስት ለመገንባትም ይረዳል ብሏል ጠቅላይ ሚንስትሩ።

በመጨረሻም የሀገራችን ብሔር፤ብሔረሰቦችና ህዝቦች የመከባበር፤የመቻቻልና በሰላም የአብሮ መኖር እሴቶቻችን ለማጠናከር መንግስት በትክረት እንደሚሰራና የመስረተልማት አውተሮችን ማሻሻል እንደምደረግም ዶር አህመድ ገልጿል።በተያያዜም ቀጣዩ ምርጫ ህዝቡ ድምጻቸው በነፃነት ለሚበጃቸው አካል መስጠት እንድምችሉና መንግስት የዴሞክራሲ ስርዓት መለኪያዎችን እንደትከተልም ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ አህመድ አብራርቷል።  

 

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>