ራሶ(cakaaranews)ሀሙስ፤ሚያዝያ 4/2010ዓ.ም.በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል በአፍዴር ዞን ራሶ ወረዳ እየተሰራ ያሉት ዘርፈብዙ የመስረተ ልማት ሥራዎችና ግንባታዎች እንደ ጠቅላላ ሆስፒታል ፤ንጹህ የመጠጥ ውሃ ዝርጋታና በፈዴራል መንግስት እየተዘረጋ ያለው የማብራት ኃይል ዝርጋታ ፖሮጀክቶች ሁሉም በታለመለት አላማና ግብ መሰረት እየተከናወኑ መሆኑና በማገባደድ ላይ እንደሚገኙም የዞኑ የአፍዴር ዞን አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ፈርሃን አብዲ ማቹን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስት የአፍዴር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ፈርሃን አብዲ የሚመራ የዞኑ ከፍተኛ አመራር አካላት በራሶ ወረዳ በክልሉና ብሎም በፈዴራል መንግስት እየተሰራ ላሉት ትላልቅ የመስረተ ልማት ፖሮጀክቶች ላይ የመስኪ ምልከታ ጎቡኝት ባደረጉበት ወቅት በራሶ ወረዳ መቀመጫ በሆነችው በራሶ ከተማ በክልሉ መንግስት እየተገነባ ያለው አጠቃላይ ሆስፒታል ግንባታ በታቀደው መሰረት እየተገነባ በመሆኑና ሆስፒታሉ ለራሶ ወረዳ ህብረተሰብና ለአጎረባች አከባቢ ማህበረሰብም ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው እንደሁም በጤና አገልግሎት ዘርፉ በኩል ያጋጠሙ የነበሩ እንቅፋቶች እንደሚቀርፍም የአፍዴር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ፈርሃን አብዲ አክሎ ገልጿል።አያይዞም በወረዳው ቀደም ብሎ የነበረውን ጤና ጣቢያ አገልግሎት አሰጣጥና የአገልግሎቱ ጥራት በመስክ ምልከታ ጉቡኝቱ መካተታቸውና ጤና ጣቢያው ትክክለኛ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም አስተዳዳሪው አስረድቷል።
በተጨማሪም በወረዳው የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽና ተጠቃሚ ለማድረግ ከዋቢሸቤሌ እየተዘረጋ ያለው የንጹህ መጠጥ ውሃ ዝርጋታ ፖሮጀክትና በከተማው እየተሰራ የሚገኘው የሃያ አራት ሰዓት የመብራት ሃይል አገልግሎት ፖሮጀክትም እየተጠናቀቁ መሆኑን ኃላፊው አክሏል።
የራሶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በሺር አብዲ ሰሀል በበኩላቸው በራሶ ከተማ እየተገነባ ያለው አጠቃላይ ሆስፒታል በአከባቢው ማህበረሰብ በጤና አገልግሎት ተደራሽነት በኩል ያጋጠሙ የነበረው ችግሮች ለማቅረፍ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትና ሆስፒታሉ በጥራትና በዘመናዊ መልኩ የተገነቡ 357 ሰፋፊ ክፍሎች ያቀፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሆስፒታሉ ግንባታ ስራዎች ለማቀላጠፍ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርጉና በተቻለ ፍጥነት እንድሁም በቀልጣፋ መልኩ በቅርቡ ለአገልግሎት እንደሚያበቁም አስረድቷል።