ጅግጅጋ (cakaaranews) ኡሁድ ጥቅምት 19/2010ዓ.ም ይህየምክክር መድረክ በክልሉ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶአብዲመሀሙድኡመር: የኢሶህዴፓ ሊቀመንበር ና የክልሉ ምክርቤት አፈጉባኤ በአቶ መሀመድ ኢሳቅ መሪነት የክልሉንአጠቃላይሁኔታ: የልማትስትራቴጂዎችን; ሰላምናደህንነትንናመልካምአስተዳደርንእንዲሁምየክልሉንየ 2010 የበጀትእቅድ በተመለከተ ከህዝቡ ጋር በሰፊው ማብራሪያ ተሰጥቶበታል::
በተያያዜም በፈዴራል ደረጃ የሰረተኛና ማህበራዊጉዳይሚኒስትሪ ሚኒስተር አቶአብዲፋታህ አብዱላሂ,; የኢ.ፈ.ዴ.ሪ. ትራንስፖርትሚኒስትሪ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ; የፌዴሬሽንምክርቤትምክትል አፈጉባኤ አቶ ራሺድሃጂእናየጠቅላይ ሚኒስተሪ ሚኒስተር በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሚንስተር ዴታ ወ/ሮ ፈርህያ ሙሃመድኡመርበመድረኩላይተሳትፈዋል::
የፈዴራል መንግስት ልዑካኑ ከክልሉ ህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ባለፉትዓመታት በአጠቃላይ የክልሉ ህዝብ በሳለፈው ታሪካዊጨለማን ታሳቢ በማድረግ የአካባቢውማህበረሰብ በክልሉእየተንቀሳቀሰላለውማህበራዊእናኢኮኖሚያዊዕድገትተሳትፎእንዲያጠናከሩና ከሌሎች የቤሔር ቤሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር የሰላም የአብሮመኖርና የመቻቻል እሴቶችን ይበልጥ እንዲያጠናክሩአሳስቧል:: በተጨማሪምበአፍሪካቀንድውስጥየሽብርተኝነትአደጋ የጋረጠውንበመከላከል የፀጥታእናየደህንነትጉዳዮችንይበልጥማጠናከርእንዳለባቸው ገልጸዋል::
በሌላበኩል በቅርቡ በኢትዮጲያ ሶማሌእናኦሮሚያ ክልሎች መካከል በተፈጠረው ደም አፍሳሽ ግጭትና በሁለቱምክልል ህዝቦችላይ ከፍተኛቁጥር ያላቸውን ማህበረሰብ መፈናቀልያስከተለው ግጭትን የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅና በማውገዝ በሁለቱ ውንድማማች ህዝቦች መካከል የነበረው የሰለምና አብሮ የመኖር ባህልን እንዲመለስና ለተፈናቃዮችም የመልሶ ማቋቋም ሥራ መስራት እንዳለበትም አመልክቷል::
በመጨረሻምልዑካኑየክልሉንመንግስት የመልካምአስተዳደርና የልማትስትራቴጂዎችንእንዲሁም የክልሉንእናየሀገሪቱንሰላምናደህንነትለማጠናከር እየተደረጉ ባሉ የህዳሴያችን ግስጋሴን አበረታቷል::