Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

የኢ.ሶ.ክ. ም/ፕረዝዳንት የደም ባንክና ዘመናዊ የመድሃኒት መስጫ ማዕከላት አስመረቀ

$
0
0

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ቅዳሜ፤ሰኔ 02/2010ዓ.ም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህብረተሠቡን ጥራት ያለውን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ የክልሉ መንግሥት በትኩረት እየሠራ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና የጤና ቢሮ ሃላፊ ገለፁ። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በጅግጅጋ የተገነባውን የደም ባንክ አገልግሎት ማዕከል እና በካራማራ ሆስፒታል የመድሃኒት አገልግሎት መስጫ ማዕከል መርቀው ከፍተዋል።

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ባለፉት ዓመታት በየደረጃው የሚገኘውን ህዝብ ጥራቱን የጠበቀና በቂ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ የጤና ተቋማትን ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች ደም የሚያስፈልጋቸውን የህብረተሠብ ክፍሎች ተጠቃሚ ለማድረግም በጅግጅጋ ከተማ የተገነባው የክልሉ የደም ባንክ አገልግሎት ማዕከል የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የጤና ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት በክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድርና ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ሀምዲ አደን እና በሲቪል ሰርቪስና ሰው ኃይል ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አህመድ ኮሬ ተመርቋል።

ግንባታው የተጠናቀቀውን እና በአስፈላጊ የጤና መሣሪያዎች የተደራጀውን የክልሉን ደም ባንክ አገልግሎት ማዕከል መርቀው የከፈቱት የኢ.ሶ.ክ. ም/ርዕሰ መስተዳድርና የጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ሀምዲ አደን ህንፃውን መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት "ይህ ዛሬ መርቀን የከፈትነው የደም ባንክ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ በጀት የተሠራ ሲሆን በዚህ አዲስ ትልቅ አገልግሎት የሚሰጥ የደም ባንክ አገልግሎት ማዕከል ለሠራተኞች የማስተላልፈውና አደራ የምለው በትክክለኛው መንገድ ህብረተሠቡን እንዲያገለግሉ ነው።"

በተጨማሪም የክልሉ  የጤና ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ አይደሩስ  አህመድ በበኩላቸው የተመረቀው የደም ባንክ ማዕከል በቀጣዩ የአገልግሎት ማዕከሉን በማስፋፋት በሌሎች ከተሞችም እንደሚከፈት ገልፀዋል። "ይህ ዛሬ መርቀን የከፈትነው የደም ባንክ አገልግሎት ማዕከል ለክልላችን ዘመናዊ እና አዲስ ከመሆኑም በተጨማሪ እንደ ክልል የመጀመሪያም ነው የዚህ አይነት የደም ባንክ አገልግሎት ማዕከላት በቀጣይ በጎዴ እና ሃርጌሌም የሚገነቡ ይሆናል ይህ የደም ባንክ አገልግሎት ማዕከል ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ይታወቃል እሱም እናቶች በወሊድ ጊዜ በደም እጥርት የሚደርስባቸውን ሞት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል በክልላችን ለሚኖሩ ማንኛውም የማህበረሠብ ክፍሎች በአስፈላጊና በፍጥነት አገልግሎትን ይሰጣል ብለን እናምናለን።"

በሌላ በኩል "በክልላችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዘመናዊ የደም ባንክ አገልግሎት ማዕከል ተገንብቶ ለአገልግሎት በመብቃቱ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል። ዛሬ የተመረቀው ይህ ማዕከል የሚሳየው በክልላችን ውስጥ ያለውን ከፍተኛ ልማትና እድገት ነው። ይህም ባለ ሁለት ህንፃ ባለቤት አድርጎናል በመቀጠልም ይኸው የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በቀጣይም በጎዴና ሃርጌሌ ከተሞችም ሥራ ይጀምራሉ።" ሲሉየክልሉ ጤና ቢሮ ተሰረተኛ የሆኑት አቶ ዙቤር ገልጿል።

በተመሳሳይ የመንግሥት ሥራ ሃላፊዎቹ በጅግጅጋ ከተማ ካራማራ አጠቃላይ ሆስፒታል የተገነባውን ዘመናዊ የመድሃኒት መስጫ መርቀው ከፍተዋል። ም/ርዕሰ መስተዳድሩ በምርቃት ሥነ ስርዓቱ ወቅት ፋርማሲው ለህብረተሠቡ በሚሰጠው አገልግሎት ጥራት ያላቸውን መድሃኒቶች ለህብረተሠቡ ለማቅረብ የሚያስችል ከመሆኑ ባሻገር የዚህ ፋርማሲ መገንባት ትልቅ ፋይዳ የመድሃኒት አገልግሎትና የመድሃኒቶችን ቁጥጥርና ለተጠቃሚው የተሻለ ግንዛቤን ይሰጣል በተጨማሪም ይሄ ፋርማሲ እንደ ክልል የመጀመሪያው ነው” ሲሉ ገልፀዋል።

በክልሉ ሲቪል ሴርቪስና ሰው ኃይል ልማት ቢሮ ሃላፊ ሃላፊ አቶ አህመድ ኮሬ "ዛሬ በካራማራ ሆስፒታል ግንባታው ተጠናቆ ለህብረተሠቡ አገልግሎትለመስጠትሲበቃ በማየቴ በእውነት በክልላችን እንዲህ አይነት ዘመናዊ ፋርማሲ ሲገነባ የመጀመሪያውና ዘመናዊ ነው ለህብረተሠቡም ከቀድሞው በተሻለ መልኩ የመድሃኒት አገልግሎቱን ተደራሽ ያደርጋል።"

 

በመጨረሻም የካራማራ አጠቃላይ ሆስፒታልሥራ አስኪያጅም በሆስፒታሉ የተመረቀው ይህ ፋርማሲ ህብረተሠቡን በቅርበት ጥራት ያለው መድሃኒት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልፀዋል። 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>