Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

12ኛው የህዝብ እና መንግሥት የጋራ መድረክ ትናንት ፣ ዛሬና ነገን በጥልቀት የመረመረበት ጉባኤ እንደነበር ተገለፀ

$
0
0

አውበሬ(cakaaranews)ቅዳሜ ፤ግንቦት 10/2010ዓ.ም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ እና መንግሥት በጋራ ያመጡት የክልሉ ዕድገት የማያስደስታቸው አካላት የተገኘውን የልማት ውጤቶች እና የህዝቡን ሠላም ለማናጋት ሌት ተቀን ቢሠሩም የክልሉ ህዝብ አፍራሽ ተልዕኳቸውን ጠንቅቆ ያውቃል ያሉት ወ/ሮ ፈርቱን አብዲ ማህዲ የኢ.ሶ.ክ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ናቸው።

12ኛው የአውበሬ የህዝብ እና መንግሥት የጋራ ምክክር መድረክ የ3 ቀናት ቆይታ የነበረው ሲሆን ህዝብ እና መንግሥት በጋራ በመሆን የክልሉን እና የሃገሪቱን የህዳሴ ለውጥና ዕድገቶችን ለማስቀጠል ቃል የተገባበት ጉባኤ ነበረ ያሉት የኢሶህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ፈርቱን አብዲ ክልሉ ያገኛቸውን የሠላም ፣ የልማት ፣ የመልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ለውጦችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል።

በተጨማሪም የሀገሪቱም ሆነ የክልሉን ሠላም እና ልማት የማይወዱ አካላት ፀብ ለማጫር የሚቃጡበትን አፍራሽ ተልዕኳቸውን በነቂስ በመውጣት ሁሌ ከመንግሥት ጎን በመቆም ከደወንሌ እስከ ሞያሌ ያለው የሀገሪቱን ዳር ድንበርን በትጋት እንዲጠብቁ  በ12ኛው የህዝብ እና መንግሥት የጋራ ምክክር ላይ የተገኙት የክልሉ ሃገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል።

በመጨረሻም በአውበሬ ወረዳ በነበረው 12ኛው የህዝብ እና መንግሥት የጋራ ጉባኤ ከ4 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን በመድረኩም ላይ መንግሥት ከህዝብ ጋር በመሆን በክልሉ የታዩ ሁለንተናዊ ዕድገቶችን አጠናክሮ እንደሚሠሩም ቃል የተገባ ሲሆን የታዩ ክፍተቶችን ለማስወገድ መንግሥት ከህዝብ ጋር በጋራ በይበልጥ እንደሚሠሩም አስታውቋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>