ጅግጅጋ(Cakaaranews)ዕሮብ፤ግንቦት 8 ቀን፤2010ዓ.ም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ለመላው የሃገራችን እስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን ሲያስተላልፉ የረመዳን ወር ጾም የተቸገሩ ወንድሞቻችንን በመተዛዘን እና በመረዳዳት መሆን እንዳለበት በመግለፅም ጭምር ነው ።
በተጨማሪም የረመዳን ወር ጾም የመረዳዳት ፣ የእዝነት ፣ የፍቅር ፣ የሰላም ፣ የደስታ እና የአብሮነት ወር በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ አቅመ አናሳ ወንድም እና እህቶቹን በመደገፍ እና የአቅሙን በማድረግ ጾሙን በመተጋገዝ በራህመት ፣ በበረከት እና በኢባዳ እንዲጾሙ አሳስቧል ፕረዝዳንቱ።
በመጨረሻም ክቡር ፕሬዝዳንቱ የሃገራችንም ሆነ የክልላችን ህዝበ ሙስሊም የረመዳንን ጾም የሰላም ፣ የልማት እና የብልጽግና እንዲሆን ዘንድ በኢባዳ እና በጸሎት እንድናሳልፍ ረመዳን ከሪም በማለት መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ ቀጣዩ የረመዳን ጾምም በሠላም፤በልማት ፤በብልጽግና እና በጤና እንዲያደርሰንም ተመኝተዋል።