Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

የጎዴ ግብሪና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ15ተኛ ጊዜ 311 ስልጠናቸው ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን አስመረቀ

$
0
0

ጎዴይ(Cakaaranews)ሰኔ,13/2010ዓ.ም.በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የጎዴይ ግብርናና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ   በ1994ዓ.ም ከተቋቋመ ጀምሮ በተለያዩ የስልጠና መስኮችን በመደበኛና አጫጭር ስልጠናዎች የሰለጠኑ  ተማሪዎችን አስመሪቆ ወደ ሥራ አሰማርቷል፡፡

ኮሌጁ የክልሉ ህብረተሰብ የሙያ ፊላጎት ለማርካት በተመለከተ በግብርናና ቴክኒክ ዘርፎች የሚተኮሩ ጥናቶችን በማድረግ በገበያ ፊላጎት ያላቸው ሙያዎች የክልሉ ወጣቶችን አሰልጥኖ ወደ ገባያ አሰማርተዋል፡፡ በዛሬ ዕለትም 311  መደበኛ ሰልጣኞችን እስከ ደረጃ አረት ብቃታቸው ከተረጋገጡ በኋላ የምረቃት ሥነ-ሥርዓት አደርጎላቸዋል፡፡ ተመራቂ ተማሪዎቹ 68 ሴቶች ሲሆኑ 243 ደግሞ ወንድ መሆናቸውን የኮሌጁ ዲን አስገንዝቧል።

በምረቃት ሥነ ስርዓት ላይ የተመራቂ ሰልጣኞችን ወላጆች፤የሸቤሌ ዞን አመራርና የጎዴይ ከተማ መስተዳደር ከንቲባ ተወካይ፤የተላያዩ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረጉለት እንግዶችም ተገኝተዋል፡፡

በምረቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሸቤሌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ አብዲ በሬ  ተገኝቶ  ሲያስተላለፉ “በዛሬው ዕለት እዚህ ቦታ ተገኝቼ የጎዴይ ግብርናና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ   የሚያስመርቁት ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ  መልዕክተን ማስተላለፈን በጣም ደስ ብሎኛል፤ ምክኒያቱም ተመራቂ ሰልጣኞችሁ ለክልላችን እድገት ያላቸው ፋይዳ የላቀ መሆኑን ከመነሳት በበኩለ ደስተኛ ነኝ” ሲሉ ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም በምረቃቱ ላይ የጎዴይ ግብርናና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  ዲን አቶ አብድቃድር  መሀመድ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸው ሲያስተላለፉ “በቅድሚያ ለዛሬው ተማራቂው ሰልጣኞችን  እንኳን ደስ አላችሁ እላቿለው ክቡራንና ክቡራት ለዚህ ቀን ለአስራአምስተኛ ጊዜ የሚትመርቁ ተማሪዎች የኮሌጃችን ዋና አላማ ስላሳካችሁ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ እላለው”፤ በሃገራችን በየዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶቻችን ቀጣይነት በማረጋገጥና የበለጠ ውጤት በማስመዝገብ ሀገራችንን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራትተርታ ለማሰለፍ የተነደፈው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በመተግበር ላይ ትገኛለች፤ ይህንን ተከትሎ ብቁ የሰው ኃይል ማፍራት የማይተካ ሚና እንዳለው በሃገር ደረጃ ግንዛቤ ተይዞ የሰው ሀብታችንን አቅም ለማሳደግ በሁሉም የሙያ መስኮች በአስተማማኝ የሰፈነባትን ሀገር ለመገንባትና የያዝ ነው የህዳሴ ጉዞ እውን ለማድረግ የትምህርትና ሥልጠና ሚና እጅግ የላቀ ነው” ብሏል

በሌላ በኩል የጎዴ ከተማ አስተዳድር ከንቲባ  ተወካይና ከተማ አስተዳደሩ የፋይናስና ኢኮኖሚ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ አያን ሀሰን  የጎዴይ ግብርናና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  ለ15ኛ ጊዜ ካስመረቃቸው ሰልጣኞች መካከል ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ለተመረቁት ሰልጣኞችን የተለያዩ የማበረታቻ ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

በመጨረሻም ተመራቂ ሰልጣኞቹ ከብዙ ውጣ ውረዶች በኋላ ዛሬ ለዚህ ምርቃት በማብቃታቻውን እጅግ መደሰተኛ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን በቀጣይም የተጣለባቸውን ሃላፊነት በአግባቡ እንደሚወጡም ቃል ገብተዋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles