ጅግጅጋ(Cakaaranews)ሀሙስ፤ግንቦት 30/2010 ዓ.ም. ቀኑ በጅግጅጋ ከተማ የፕላስቲክ ፅዳት የማኔጅመንት ተማሪዎች የግንዛቤ ውይይት ተጀምሮ በካራማራ ተራራ የ400 ችግኞች ተከላ ሥነ ሥረዓት በማድረግም ስለመጠናቀቁ ተገለፀ። ከአንድ ቀን በፊት ነበረ እ.አ.አ. ጁን 5 በዓለምአቀፍ ደረጃ ለሚከበረው የአካባቢ ጥበቃ ቀን ምክንያት በማድረግ የኢ.ሶ.ክ.የአካባቢ ጥበቃ፤ማዕድን፤ኢነርጂና ደን ልማት ኤጀንሲ ከፅዳት ዘመቻው ባለፈ በክልሉ የሲቪል ሴርቪስና ስራ አመራር ኮሌጅ ተማሪዎች ስለ አከባቢ ጥበቃ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የተሰጠው።
ታዲያ እለቱ ታስቦ በሚውለበት ቀንም የክልሉ የአካባቢ ጥበቃ፤ማዕድን፤ኢነርጂና ደን ልማት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ በአጠቃላይ የኤጀንሲው ሠራተኞች ወደ ጅግጅጋ ከተማ ዕምብርት መዝለቂያ አፋፍ ላይ በሚገኘው ካራማራ ተራራ ላይ 400 የሚደርሱ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ችግኞችን የተከሉት።
የችግኝ ተከላውም “በክልሉ የሚታየውን የተፈጥሮ ጥበቃ አደጋ በጋራ እንከላከል” በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን ከችግኝ ተከላ በኋላም የኢ.ሶ.ክ የአካባቢ ጥበቃ፤ማዕድን፤ኢነርጂና ደን ልማት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መውሊድ ሃይር እለቱ ስላለው ትልቅ ፋይዳና ጠቀሜታ "ዛሬ እያከበርን ያለነው ዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ቀንን ነው በዓሉን በሶስት አብይት ጉዳዮች ላይ አትኩረን እያከበርን እንገኛለን ሰሞኑን እንደተመለከታችሁት በከተማችን ጅግጅጋ ፅዳት ላይ ስንሠራ ነበር እሱም በተለይ ፕላስቲኮች በክልሉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ እንደመሆናቸው መጠን እነሱን የማስወገድ ሥራ ሲንሠራ ነበር። ዛሬ ደግሞ እዚህ ካራማራ ተራራ ላይ የችግኝ ተካላ እያካሄደን ነው በዚህም ሥራ እንደሚታየው ተራራው አረንጓዴ መልበስ ችለናል ከተራራው በሚራጊፈው ፍሬም እርስ በርሱ እየተባዛ ይገኛል። ሌላው ከዚሁ ጋር ተዛማጅ የሆነውን የባዮጋዝ ሥራ ነው፤ ባዮጋዝ ከከብቶች የሚገኝእዳሪ ኩበት ሃይል ሲሆን ምግብን ከማብሰል በዘለለ፤ ለመብራት ኃይልነትም ያገለግላል ከሱ የሚወጣው ተረፈ ምርት ደግሞ ለአትክልቶችና ለእርሻ ማዳበሪያነትም ይጠቅማል ሁለም ጠዋት ጠዋት እስከ 20 ሊትር የሚደርስ ውሃ የሚናጠጣ ሲሆን በርካታ ተረፈ ምርትም ይገኝበታሉ"ሲሉ ገልፀዋል።
በተጨማሪም የኢ.ሶ.ክ የአካባቢ ጥበቃ፤ማዕድን፤ኢነርጂና ደን ልማት ኤጀንሲ ም/ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱረዛቅ ጠይብ "አጀንሲው በአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚያደርገው ተግባራትና አሁን በከራማራ ተራራ ላይ የሚናካሄደውን የችግኝ ተከላ ለ2ኛ ጊዜ ሲሆን በአከባቢው የአየር ንብረት ለውጥ የራሱ የሆነ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሊያደርግ እንደሚችል የተሠሩት ሥራዎች በግልፅ ያሳያሉ” ሲሉ አብራርቷል። አያይዞም የችግኝ ተከላ ሥራ ከአሁን በፊት በከተማ ብቻ ሲሰራ እንደነበርና አሁን ግን በተራራዎች አከባቢም እንደሚሰራና ለአከባቢ ጥበቃም ምቹ ሁኔታን እንደምፈጥርም አቶ አብዱረዛቅ አስረድቷል።
በጅግጅጋ ከተማና በአጠቃላይ በሀገራችን ለ25ተኛ ጊዜ የተከበረውን የአካባቢ ጥበቃ ሥራም ላይ የከተማው ከንቲባ ፅ/ቤት ሰረተኞች፤አመራር አካላትና የክልሉ ሲቪል ሴርቪስና ስራ አመራር ኮሌጅ ዲንና ተማሪዎች እንዲሁም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችም ተሳታፊ ሆነዋል።