Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

በኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑካን ቡድን የኢሶ.ክ. መ.መዲና ደርሷል (2)

$
0
0

ጅግጅጋ(Cakaaranews) ቅዳሜ፣ መጋቢት 29/2010ዓ.ም. በኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራ ከፍተኛ የፈዴራል መንግስት ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ርዕሰ መዲና ደርሷል።በልዕኳን ቡዱኑ መካከል የኢፈዴሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የኢህኣዴግ ማዕከላዊ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሺፈራው ሺጉጤ፣ የኢፈዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፣ የኢፌድሪ የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ከበደ ጫኔ ፤የኦሮሚያ ክልል ርዕሰመስተዳደር ክቡር አቶ ለማ መገርሳ፤በኢፈዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዲብለማሲ ጉዳዮች ዳይረክተር አምባሳደር መሀሙድ ድሪር እና ሌሎች የፈዴራልና የክልል መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣናት በጅግጅጋ ከተማ የሚገኘው ገራድ ውልዋል ዓለም ኣቀፍ የኣየር ማርፊያ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ 

በተጨማሪም በኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው ከፍተኛ የመንግስት ልዑካን ቡድን በጅግጅጋ የሚገኘው የገራድ ውልዋል አለም ኣቀፍ አየር ማርፊያ  ሲደርሱ የኢ.ሶ.ክ.መ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር፣ የኢፈደሪ የትራንስፖርት ሚኒስትር  አቶ አህመድ ሺዴ፣ የኢፈደሪ  ሰረተኛና መህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ አብዲፈታህ አብዲላሂ፣ የኢ.ሶ.ክ.መ ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ በፌዴራልና በክልል ደረጀ ያሉት ከፍተኛ ባለስልጣነት፣ የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ በክልሉ ፖሊስ ማርሽ ባንድና የባህል ቡድኖች በማጀብ ደማቅ የአቀባበል ሥነ-ስርዓት ተደርጎላቸዋል፡፡

በተያያዜም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው ከፍተኛው የመንግስት ልዕኳን ቡድኑ በአየር ማርፊያው እንግዳ ማረፊያ ክፍል የተወሰነ ደቂቃዎች እረፍት ከወሰዱ በኋላ ብዙሃኑ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ማህበረሰብ በመንገዶቹ ዳር ቆመው ደማቅ አቀባበል እያደረጉላቸው፣ በእግረ መንገዳቸው ለክልሉ መንግስት ካቢኔ አባላትና ለስራ ሃላፊዎች በክልሉ መንግስት በጅግጅጋ ከተማ በዱልቀበው ሰፈር የተገነባላቸዉን  ዘመናዊ መኖሪያቤቶች ጎብኝት በማድረግ ወደ ክልሉ መስተዳደር ፅ/ቤት አቅንቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ልዕኳን ቡድኑ የመስተዳደር ፅ/ቤት ከደረሱ በኋላ በቅርቡ በክልሉ መንግስት የተገዙት ዘመናዊ የእሳት አደጋ ቦቴዎችን ጎብኝቷል።በመስኪ ምልከታ ወቅትም የኢ.ሶ.ክ .መ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር የዘመናዊ ቦቴዎቹ ጥራትና የአገልግሎት አሰጣጠቸዉን መብራርያ በመስጠት፤በመስተዳደር ፅ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ከ95% በላይ ከአፈር የተሰረዉን ቤትም አስጎበኝቷል፡፡ አያይዞም የክልሉ ፕሬዝዳንት የአፈር ቡሉኬት ማምረቻ ማሽኑን በክልሉ ያሉት ወረዳዎችን እንደተከፋፈለላቸውን ኣክሎ ገልጿል፡፡

በተመሳሳትም ልዕኳን ቡዱኑ ወደ ሰብሰባ አዳራሽ ከመግባታቸው በፊት ለትዳር የታጩት ባልና ምስቶች የተዘጋጀላቸዉን ማረፊያ ቦታ ጎበኙ፤ ስላሙሽራዎችን ፅንስ ሀሳብና አላማ ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ም/ቤት አፈ ጉባኤና የኢሶህዴፓ ሊቀመንበር ክቡር አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅ እና የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ሲሆኑ ይህ ታሪካዊ የትዳር ትስስር ለዘመናት ግፊ ሲመሰርትባቸውና ሲጮቆኑ የነበሩት የገቦዬ ማህበረሰብ ከመላው የሶማሌ ህዝብ ዘንድ ሲገለሉና አድሎ ሲደረጉበቸው የከረሙ እንደ ነበሩ ገለፃ በመስጠት፤ በራሶ ወረዳ የተደረገው የክልሉ መንግስትና  ህዝብ የጋራ ምክክር ጉባኤ ላይ በሰፍው ተወያይቶበት፣ በክልሉ ጎሰ መሪዎችና የኀይማኖት አባቶች እንደሁም ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ታዳሚዎች በተገኙበት መድረክ ይህ የኋላቀርነት አስተሳሰብ በጭራሽ ከመሀላችን እንዲወገድ የተስማማንበት መድረክ እንደ ነበረም ኣክሎም ገልጿል፡፡  አያይዞም ይህን የኋላ ቀርነት አስተሳሰብ ለማስወገድ የተጠቀመበት መጀመሪያ ስልት ከገቦዬ ጎሳና ከሌሎች የኢትዮጵያ ሶማሌ ጎሳዎችን መካከል የእርስ በእርስ በትዳር እንድተሳሰሩ በማድረግና እንደ መፍትሄ የተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩልም ሙሺራዎቹ በበኩላቸው የተሰማቸው ደስታ በኢፈዴሪ ጣቅላይ ሚኒስትር የሚመራው ልዕኳን ቡድን በመድለጽ፤ የክልሉ መንግስትና መሪው ድርጅት ኢሶህዴፓ የሚያደርጉት ታሪካዊ የትዳር ትስስር ምንግዜም በሶማሌ ህዝብ ዘንድ የማይረሳ ወርቃማ አጋጣሚ መሆኑንም አስረድቷል።በተጨማሪም መንግስት በራሶ ወረዳ ላይ የገበዉን ቃል በተግበር አሰይቶናል፣ ይህ ደግሞ የክልላችን መንግስት ለህዝቡ ያለዉን ፍቅር እንደሆነም አስታየት ሰጭዎቹ ተናግረዋል፡፡

 

 

 

 

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>