Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

በክልሉ ርዕስመዲና በጎጂ ልማዶች የሚትኮር የሲምፖዝየም መድረክ ተጀመረ

$
0
0

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ሰኞ ታህሳስ 23ቀን/2010ዓ.ም.በክልሉ ርዕስመዲና በመስተዳደር ጽ/ቤት ጊቢ በሚገኘው በካሊ1 አደራሽ በጎጂ ልማዳዊ ድርግቶች የሚወያይበት የሲምፖዝየም መድረክ  ተጀመረ።በምክክር መድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመረር አባላት የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድና የክልሉ ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅን ጨምሮ የክልሉ ካቢኔ አባላት፤አገር ሽማግሌዎች፤የሃይማኖት አባቶችና የክልሉ ሴክተር መ/ቤቶች ሰረተኞችና ሌሎች እንግዶችም ተገኝቷል።

በመድረኩ መፍቻ ላይ በክልሉ ልማት፤ሰላምና በክልሉ መልካም አስተዳደር ህደቶች ዙሪያ አጭር ርፖርት ያቀረቡት የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር የሲምፖዝየሙ አላማ “በክልሉ የሚኖሩ ጎሳዎችን መካከል በአንዳንድ ጎሳ ላይ የሚደረገው ጎጂ ንቀቶችን ለማስወገድ፤በክልሉ ማህበረሰብ ውስጥ የሚታዩ ጎጂ ልማዳዊ ድርቶች እንደ የሴት ልጅ ግርዛትና ስራን የመናቅ፤ እንድሁም የነዋሪ ማተወቅያ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን ለማጥፋት የሚወያይበት ሲምፖዝየም መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም በክልሉ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ለሚጠቀሙት የንቀትና ጸያፍ ቃላት መቆም አለባቸው በማለት ለምሳሌ ያህል በአንዳንድ ማህበረሰብ ላይ የሚጠረው ስያሜዎችና በሶማለኛ ቋንቋ “ሚድጋን” የሚለው ቃል በድሮ በእንስሳት አደን ጊዜ ሲጠቀሚበት የነበረ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ቀስት ማስቀየስ”ሲሆን “ገቦያ” የሚለውም “የቀስት መያዣያ” እንደሆ “ቱማል”የሚለው ቃልም “ተከሻ ተጠቀሞ የበላ ወይም ቀጥቃጭ” የሚል ትርጉም የሚሰጡ  የንቀት ቃላት ከመሆናቸው ባሻገር እንደዚህ አይነት የንቀት ተግባራት ተቀብሎ እራሳቸው ዝቅ ያደረጉት ጎሳዎች ከመሰረቱ እራሳቸው የናቁና የበታች ያደረጉ እራሳቸው ናቸውና የሰው ልጅ ሁሉ እኩል እስከሆነ ድረስ መቀበል አልበረባቸውም  ብሏል የክልሉ ፕሬዝዳንት።

ፕሬዝዳንቱ እንደ የሴት  ልጅ ግርዛት ያሉ ጎጂ-ልማዳዊ ድርቶች በአማራና በደቡብ ክልሎች የሴትልጅ ግርዛት በፍጹም የሴቷ ብልት ጭራሽ አይነካና በጫፉ ትንሽ ይጨረፍ ላይ ሲከራከሩ በክልላችን ደግሞ ሴቷ ሙሉ በሙሉ ትገረዝ ወይም ትሰፋ በሚል ላይ እንከራከራለን ሲሉ ተናግሯል።በተጨማሪም የክልሉ እምነት አባቶች በሴት ልጅ ግርዛት ዙሪያ ያለው ተጨባጭና ግልጽነት ያለው እምነታዊ ማስረጃ እንድያቀርቡ ፕሬዝዳንቱ አሳስቧል።

በሌላ በኩል የክልሉ ርዕስመስተዳደር በነዋሪ ማታወቅያ መስጠት ዙሪያ ችግሮች እንዳሉ ከመግለጹ ባሻገር በአንዳንድ የክልሉ ወረዎች ላይ ፎቶቤት እንደለሌና ችግሮቹ በቅርብ ጊዜ በአንድ ወጥነት ያለው መንገድ እንደሚፈቱ ጠቆሟል በተጨማሪም ፎቶቤት የሌላቸው ወረዳዎች ለአከባቢው ወጣቶች የፎቶቤት መሳሪያዎች ተገስቶለት የስራ እድል እንደሚፈጠርላቸው እና ማህበረሰቡም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ፕሬዝዳንቱ አብራርቷል።

በመጨረሻም የክልሉ የሃይማኖት አባቶች በበኩላቸው የአንድ ጎሳ/የማህበረሰብ ክፍል የመናቅም ሆነ በጎጅ ልማዳዊ ድርግቶች እንደ የሴት ልጆቻችን ግርዛት በእስልምና ሃይማኖት በቁርዓንም ሆነ በሀዲሲን የማይፈቀድ ምንጭ አልባ ተግባራት መሆናቸውን ገልጿል።የሲምፖዝምየም ውይይቱ ለቀጣይ ቀናት እንደሚቀጠልም ተገልጿል።

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>