Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

10ኛው የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ የጋራ ምክክር መድረክ በስኬት ተጠናቅቋል

$
0
0

ጅግጅጋ(Cakaaranews) ሰኞ ጥቅምት 20/2010ዓ.ም. ላለፉት 5ቀናት ቀናት በጅግጅጋ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተውና የክልሉልማትሰላምናመልካምአስተዳደር እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር ታስቦ የተዘጋጀው የጋራ መድረክ ዛሬ በስኬት ተጠናቅቋል፡፡በካሊ አደራሽ በተዘጋጀው በዚሁ መድረክ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት የክልሉ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶአብዲመሀሙድና የኢትዮጵያ ሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሳዊ ፓርት (ኢሶህዴፓ) ሊቀመንበር እና የክልል ምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ መሀመድረሼድ ኢሳቅ መብራሪያ ተሰጥተዋል፡፡

በመዝጊያ ሥነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ለመድረኩ ተሳታፊ  አገር ሽማግሎች፣ ወጣቶች ፣ ሴቶችና ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አካላት ለነበራቸው የላቀ ተሳትፉ ከፍ ያለ ምስገና አቀርቧል፡፡

የክልሉ ህዝብና መንግስት የሀገራችንም ሆነ የክልሉን ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም መልካም አስተዳደርን ለማስፈፀም ለሚያደርገው ሁለንተናዊ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀርቧል፡፡

የክልሉ ህዝብ ዋነኛ ጠላት የሆነው ድህነትን ለማጥፋትና በሁሉም ዘርፍ ራሴን ለመቻል መንግስት የነደፈው እቅድ ውጤታማ በማድረግ ከህዝቡ ተሳትፎ ውጪ ሊታሰብ የሚቻል ጉዳይ እንዳልሆነ አስምሮበታል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎችአገር ሽማግሌዎች የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ለማጠናከር የሚረዱ የጋራ የስምምነት ነጥቦች አቀርቧል፡፡ከእነዚህ መካከል፤1ኛ ከጽንፈኝነት አክራሪነትና ከአሸባሪነት አመለካከት ጋር ለመታገል እንደሚሰሩ 2ኛ የክልሉ ህዝብና መንግስትም ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ወገኖች በዘላቂነት ለማቋቋም የሚደረገው ጥረት ለአንድ አፍታ ያህል እንዳማይቆምና የተፈናቃይ ወገኖች ኑሮ ወደ ነበሩበት መደበኛ ኑሮ ለመመለስ ድጋፍ እንደሚያደርጉ 3ኛ የክልሉ ህዝብ ራሱን እንዲችል የሚያግዝ እና በውሃ፣ በእንስሳት መኖ፣ በጤናና በትምህርት መሰረት ያደረገው የክልሉ እቅድ በቁርጠኝነት እንደሚያሳኩና 4ኛ በሥራ እድል ፈጠራ የሚያተከረውና የሥራ ክቡርነት ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ለመገንባት ዓለማ ያደረገው ‘ተዓብና ማል’ ኢንተርፕራይዝ የክልሉ ወጣቶች በሰፊው እንዲሳተፉ ግንዛቤ እንደሚሰጡ አረጋግጧል፡፡ 

በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ኣወዳይ ከተማ ህይወታቸው ላጡ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጅ ቤተሰቦች ለማቋቋሚያ የሚውል ለእያንዳንዱ ቤተሰብ የ500,000 ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ ከተፈናቃይ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተረክበዋል፡፡

የመድረኩ ተሳተፊዎች በክልሉያለው የሰላም፣  የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ያላቸው ተሳትፎበማጠናከር ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በሰላም አብሮ መኖር እና የመቻቻል የቆየ እሴቶቻችንን ይበልጥ እንዲጎለብቱ ከምን ጊዜውም በላይ እንደሚጠበቁ እንዲሁም ለህገ- መንግስታችንና ለፈዴራሊዝም ሥርዓታችን ቀጣይነት ዘብ እንደሚቆሙ ቀል ገብቷል::

በመጨረሻም በሥነ ስርዓቱ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ያተረፈው ታዋቂው የሙዜቃ ባለሙያና በሶማሊማህበረሰብ ዘንድ ክብር የሚሰጠው አንጋፋው አርቲስት አህመድ አሊ ኢጋል ለመድረኩ ተዳሚዎችሁ አዝናኝ ሙዚቃ በማቅረብ አዝናንተዋል፡፡

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>