Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የገጠር መንገዶች ግንባታ የስኬትጉዞ!

$
0
0

 

Jigjiga(Cakaaranews)  ማክሰኞ መስከረም 23,2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ከአንባገነኑ ደርግ ውድቀት በኋላ በሀገሪቱ በተፈጠረው ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ እራሱን በራሱ ለማስተዳደር በሕገ-መንግስቱ የተረጋገጠለትን መብቶች በመቀበል ከቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በመፈቃቀድና በመከባበር ላይ በተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ውስጥ እየኖረ ሲሆን በዚሁ መሠረት የሶማሌ ክልል ህዝብ ህገ-መንግሥቱ ባጎናጸፋቸው መብቶች ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በኢኮኖሚያዊ፤ በማህበራዊ፤ በፖለትካዊና እንዲሁም በፍትህ፤ በሰላም፣ ዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ዘርፎች አመርቂ ውጤቶች አስመዝግቧል፡፡

 

በዚሁ መሠረት በመሰረተ ልማት ዘርፍ በተመለከተ ክልሉ ካስመዘገባቸው ውጤቶች ውስጥ መንገድን በተመለከተ በክልሉ ያሉትን መንገዶች በፌድራል የሚሰሩ መንገዶች፣ በክልል የሚስሩ መንገዶች እና የአከባቢዉ ማሕበረስብ (በክልሉ ህዝብ ተሳትፎ ) የተሰሩባቸዉ መንገዶች የሚከፋፈ ሲሆን በአጠቃላይ የመንገድ ርዝማት በ2002  ከነበረበት ከ1000 ኪሜ በመነሳት በ2009 ዓም ወደ 17600 ኪሜ ለማሳደግ ተችሏል፡፡

 

ከነዚህ መካካል 5096ኪሜ በአጠቃለይ በክልሉ አቅም የተሠሩ፣ መንገዶች ርዝመት 10200ኪሜ ደግሞ የአከባቢዉ ማሕበረስብና ህዝባዊ በሆነው ልዩ ፖሊስ አመከኝነት በጋራ የተሰሩ ናቸዉ ፡፡

 

ይህንኑ የመሠረተ ልማት ስራ የበለጠ ለማቀላጠፍና በተሻለ ጥራት፣ ጊዜ እና ወጭ እንድሰራ ለማድረግ ክልሉ የተለያዩ ኢንተርፕራይዞችን ማለትም የሶማሌ ክልል ልዩ ኢንተርፕራይዝ፣ ድዛይንና ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ እና የመንገድ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የቋቋመ ሲሆን የተቋሞቹ ዋና ዓላማዎች ደግሞ በክልሉ የሚካሄዱ ግንባታዎች የክልሉ የመስፈፀም አቅም በላቀ ደረጃ ማስፈፀም ነዉ፡፡

 

የክልሉ መንግስትም ለተቋሞቹ መሽነሪና አስፈላግዉን ግባአቶችን አሞልቶላቸው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በተያያዜም የክልሉ መንግስት በሰርቬይ፣ ድዘይን እና ቁጥጥር ራሱንችሎ በመስፈፀም ላይ ይገኛል፡፡

 

በሁለተኛ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሰረት የክልሉ መንግስት ዋና ትኩረት መስጠት ላይ የአዳረገው ድልድዮችን መገንበት እና ህዝቡን ከህዝቡ ጋር መስተሳሰር የሚችል መሰረተ ልማቶችን ተደራሽነት መድረግ ላይ ነው፡፡ከዚህ ጋር ተያይዞ በክልሉ የተገነቡ ዋና ዋና ድልደዮቹም የወንጌይ ድልድይ፣ ጌልዶህ ድልድይ፣ ሶራ ድልድይ፣ ሙላ ድልድይ፣ ቆራም ድልድይ፣ ደገህመደው (ኮርኡኤሊስ) ድልድይ እና ከቀብሪደሀር ድልድይ ተሰርተው ለህዝቡ አገልግሎት መብቃት ተችሏል፡፡

 

ከዚህ በፊት የክልሉ ህዝብ ብዙ ችግሮችን ሲያጋጥመው የነበረ ከመሆኑም በሻገር የክልሉ ህዝብ ከአንድ ወረዳ ወደ ሌላ ወረዳ ለመምጣት ረዥምና ዙሪያ ጥምጥም ጉዞ በመሄድ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዳያደርግ የቆየ ነበር ፡፡

 

በአንደኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብመንገድ ለማገኘት ይወስድበት በአማካይ 30ኪሜ የእግር ጉዞ የነበረው ወደ 15ኪሜ መቀነስ ተችሏል ፡፡ በሁለተኛ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሰረት ደግሞ ወደ  5ኪሜ ለመቀነስ ተቅዶ፤ የተቀደዉ ምግቡን መምታት ችሏል፡፡

 

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በኤረር ዞን ሥር ከሚገኙ ወረዳዎች ሙሉሙልቆና ፊቅ ወረዳዎች የሚገኙ ህዝብ ከዚህ ቀደም በነበረው የመንገድ መሰረተ ልማት እጦት ሳቢያ ከዞኑ መስተዳር ጋር የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዳያደርግ እንቅፋት ሲፈጥርበት የነበረ ከመሆኑም ባሻገር በየጊዜው ሁለቱ ወረዳዎች ከኦሮሚያ መስተዳድር ጋር በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች በሚከሰቱት ግጭቶች ሳቢያ መሸሺያ በማጣት ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊች ችሮች ይዳረጉ ነበር ፡፡

 

ለአብነት ያህል በሀመሮ እና በለገሂዳ ወረዳ የአለውርቀት 70 ኪሜ ሲሆን፤ በሁለቱም ወረዳ መሀል የሸቢ ሸበሌ ወንዝ ያልፍበታል፡፡ሆኖም ግን በለገሂዳ ወረዳ የሚኖሩ የክልሉ ህዝቦች ከክልሉ ህዝብ ጋር ለመገናኘት 3200 ኪሜ ደርሶ መልስ ይወስድበት ነበር ፡፡ በዚህም መሠረት በክልሉ መንገዶች ባለስልጣን ባለቤትነት እንድሁም የመንገዶች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራያዝ አስፈፃሚናት እና በክልሉ ዲዛይንና ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ አመካሪነት በኤረር ወንዝ ላይ በተገነባው ድልድይና እንዲሁም የመሬት አቀማመጡ ተራራማ፣ ሸለቆዋማና ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የነበረውን የመንገድ መሰረተ ልማት በመገንባት በሁለቱ ወረዳዎች የሚኖሩት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ከዞን መስተዳድሩ ጋር በቀላሉ እንዲገናኙ በማድረግ ከዚህ በፊት ይገጥማቸው የነበሩትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመቅረፍ የተቻለ ሲሆን የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አብዲ መሐሙድ ዑመር የተገነባውን የመንገድ መሠረተ ልማት አስመርቀው በይፋ ከፍቷል፡፡

 

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የመንገዶች ግንባታ ስኬት ጉዞ ለመስቀጠል በ 2010.ም በእቅድ ላይ ያሉ በርካታ መንገዶች እና ድልድዮች ተቅዶ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

 

ከታቀዱት መንገዶች መካከል 98ኪሜ የሚሆን ከጅግጅጋ-ሲቲ ዞን መንገድ፣ 240ኪሜ የሚሆን አራርሶ-ዩኣሌ-አዋሬ-ዲግ ወረዳዎች የሚያስተሳሰር ፣ የ250 ኪሜ የጉረዳሞሌ-ቀርሰዱለ፣ 75ኪሜ ደግሞ በሁደት-ደዋወንዝ፣ 115 ኪሜ የሚሆን በቆልማዮ-አነበደን፣ 65ኪሜ የሚሆን የደገህቡር-ደገህመደው መንገድ፣ 28ኪሜ የሚሆን ሽላቦ-ኤርጉድበን፡፡ ከተቀዱት ድልድዮች ደግሞ የዳዋ ድልድይ፣ጎድ ኡስቦ ድልድይና የቁቢ ድልድይ ናቸው፡፡

 

ከዚህ ተያይዞ በፌዴራል መንግስት የሚከናወኑ የአስፋልት መንገዶችም ይገኙበታል፡፡ በአጠቃለይ ይህን ውጤት ለስኬት የአጎናፀፉት የክልሉ መንግስት ለለውጥ የሚያቅድ፣ ርዕይና ግብ በመቅረፅ፣ ዕሴትና ስልት መንደፍና የክልሉ ህዝብ አሳሚኖ መስራት የሚችሉ አመራር በማፍራት፣ የክልሉ ህዝብ ተሳትፎና ህዝባዊ በሆነውን ልዩ ፖሊስ አመከኝነት በጋራ የመጡ ውጤቶች ናቸዉ ፡፡

 

ጀማልአሊ፡-ነፃ ፀሃፊ

 

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>