Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

በኢሶ.ክ.መ. ርዕሰ መዲና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ደማቅ የድጋፍ ሠልፍ ተደረገ

$
0
0

ጅግጅጋ(Cakaaranews)እሁድ፤ሰኔ 17/2010ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው ጅግጅጋ ከተማ በዛሬው ዕለት የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀመድን ጨምሮ የክልሉ የመንግሥት ከፍተኛ  አካላት በተገኙበት ለክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በአማረና ደማቅ ሁኔታ የድጋፍ ሠልፍ መካሄዱ ተገለፀ።

ዛሬ እለትም የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ ከንጋቱ 12 ሠዓት ላይ የከተማዋን ጎዳናዎች ሞልተው ለክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የድጋፍ ሠልፍ ወደ ሚያደርጉበት ጅግጅጋ ስታዲዮም መታደም ጀመሩ። ቁጥራቸው እጅግ በርካታ የሆኑ የክልሉ  ወጣቶች ህብረት የሆነው ሄጎ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት (የወጣት ማዕበል)፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ በተለይ የሶማሌ ሴቶች ለየት በሚለው እልልታቸውን ጨምሮ ህፃናት እና የተለያዩ የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ድጋፋቸውን መግለፃቸው የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

በተጨማሪም የክልሉ ወጣቶች “በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከሚመራው የፌዴራል መንግስትና አቶ አብዲ መሀሙድ የሚመራው የክልሉ መንግስት ጎን ለዘላለም አንለይም”᎓᎓ “መቼም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እንደግፋለን ከጎኑም እንቆማለን” በሚል መፈክሮች እና ሌሎች  የተለያዩ አገር አንድነትን የሚያሳዩ መሪ ቃላት ይዞ ነው የታደሙት ።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢ.ሶ.ክ.መ. ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀመድ ኡመርጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ከተመረጠ ወዲህ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሃገሪቱ በርካታ ስኬቶች፣ የብሔራዊ መግባባት እርምጃዎች እና ተግባራት እንደተፈጠሩ እንደተፈጠረ የማይካድ ሀቅ ሲሆን በዶ/ር አብይ አህመድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚኒስትር የሚመራውን የለውጥ እንቅስቃሴ ያለውን አድናቆት በመግለፅ ቀጣይ አንድነታችንን ለማጠናከር የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ከግብ ለማድረስ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥትና ህዝብ ከሃገራችን ህዝቦች ጎን በመቆም እንደሚሠራም አረጋግጣለው ብሏል።

አያይዞም ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የጀመረችውን ሃገራዊ መግባባትን በማጠናከር የተሻለች ሃገር ለመገንባት በሚደረገው ትግል የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ እና መንግሥት በዶ/ር አብይ አህመድ ከሚመራው የፌዴራል መንግሥታችን ጎን እንደሚቆምም ክቡር ፕሬዝዳንቱ ገልጿል።

በዚህም ሁሉም በትላንትናው እለት የድጋፍ ሠልፉን ለማክሸፍ በንፁሃን ዜጎች ላይ የደረሠውን አስጸያፊ የቦምብ ጥቃት እንደሚያውገዛቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በትላንትናው እለት የደረሠውን አደጋ ተከትሎ የክልሉ መንግት:የሃገር ሽማግሌዎች᎓ገራዶች᎓ኡጋሶች᎓ሱልጣኖችና የእምነ አባቶች  ለክቡር ጠ/ሚኒስትሩ ድጋፉን የገለፀ ሲሆን በተጎዱ ለሟች ቤተሠቦችና ዘመድ ወዳጆቻቸው መፅናናት ተመኝተው በዜጎቻችን ላይ አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙትም አሸባሪዎች በጠንካራ አቋም እንደሚቃወሙትም ሰልፈኞቹ ገልፀዋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>