Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

በኢ.ሶ.ክ የአየር ንብረት በሚያስከትለው ለውጥ ለድርቅ ተጋላጭ ለሆኑት በኦሰትሪያ መንግሥት የሚደገፍ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

$
0
0

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ቅዴሜ፤ሰኔ 16/2010ዓ.ም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የአየር ንብረቱ የሚያስከትለውን ለውጥ ተከትሎ ለድርቀ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሠብ ክፍሎች የኑሮ መሠረታቸውን ለመደገፍ፣ ለማቋቋም እና አቅማቸውን ለመገንባት የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ።

በተጨማሪም በዋርዴር እና ቀብሪደሀር ወረዳዎች ለድርቀ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሠብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚተገበረው ይህ ፕሮጀክት ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃለፊዎች፣ የሚመለከታቸው ሴክተር መ/ቤቶች፣ ለጋሽ ድርጅቶችና የተለያዩ ሲቪክ ማህበራት በተገኙበት በፕሮጀክቱ ዙሪያ የምክክር ዓውደ ጥናት መካሄዱ የክልሉ ውሃ ሃብት ልማት ቢሮ ገለፀ።

በዚህ የምክክር ዓውደ ጥናት ላይ የፕሮጀክቱን አስፈላጊነት፣ ጠቀሜታና አተገባበር በተመለከተ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የውሃ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ አብዲ ማብራሪያ በሰጡበት ወቀት "የዛሬው የምክክር ዓውደ ጥናት በሃገራችን ድርቅ በተደጋጋሚ ከሚከሰትባቸው ክልሎች መካከል በተለይ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ተጠቃሽ ነው። የዚህ ፕሮጀክት ድጋፍ የተገኘው ከኦስትሪያ መንግሥት ሲሆን በጀቱም ከ300 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ መሆኑ ገልጿል። ይህ ፕሮጀክት ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት(UNDP) እና የዓለም የእርሻ ድርጅት(FAO)ጋር በመተባበር የሚተገበር ይሆናል። በተለይ በክልሉ ዶሎ እና ቆራሄይ ዞኖች በሚገኙት ቀብሪደሀርና ዋርዴር ወረዳዎች አከባቢ የሚኖሩ የህብረተሠብ ክፍሎች በተደጋጋሚ ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ በመሆናቸው ድርቅ የመቋቋም አቅማቸውን ለማሳደግ እና ህብረተሠቡን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል ፕሮጀክት ሲሆን በቀጣይም 

 

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>