Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

የቀብሪደሀር ከተማ የአዕምሮ ህሙማን ህክምና መስጫ ማዕከል ግንባታው መጠናቀቁ ተገለፀ

$
0
0

ቀብሪደሀር(Cakaaranews)ሐሙስ፤ሰኔ 14/2010ዓ.ም  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ቆራሄይ ዞን ቀብሪደሃር ከተማ የተገነባው የአዕምሮ ህክምና መስጫ ማዕከል በሆስፒታሉ አንድ አካል ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን ማዕከሉ የክልሉ ጤና ቢሮ ከቆራሄይ ዞን ተወላጅ ሴት ዲያስፖራዎች ጋር በመተባበር ያስገነቡት እንደሆነ ተገልጿል። የዚህ ማዕከል መገንባት በዞኑ ሆስፒታል ላይ የነበረውን ጫና እንደሚቀንስም የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።

በማዕከሉ ምርቃት ሥነ-ስርዓት ላይም የቆራሄይ ዞንና የቀብሪደሃር ከተማ መስተዳድር አመራር አካላትን ጨምሮ የዲያስፖራ ተወካዮች እና የከተማው ነዋሪዎች መገኘታቸው ተገልጿል። የማዕከሉን መገንባትና አገልግሎት አስመልክቶ የቆራሄይ ዞን  ሊቀመንበር ተወካይና የቀብሪደሃር ከተማ ከንቲባ በማዕከሉ መገንባትና ለአገልግሎት መብቃቱን እጅግ በጣም ደስተኛ መሆናቸውን አስረድቷል። ለዚህ ስኬት በውጪ ሃገራት የሚኖሩ ሴት የቆራሄይ ዞን ተወላጆች በራስ ተነሳሽነት እና በተጨማሪም በክልሉ እየታየ ላለው ዘርፈ ብዙ ልማት ከክልሉ መንግሥት ጎን በመሆን አጋርነታቸውን ለማሳየት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርክት በመቻላው እንደተደሰቱ በማመስገን ገልፀዋል።

ከሴት የዲያስፖራ አካላቱ ተወካይ ሆነው የተገኙትም በማዕከሉ ግንባታ መጠናቀቅ እና ለአገልግሎት መብቃት መደሠታቸውን ገልፀው ይህንን ማዕከል ለክልሉ ጤና ቢሮ ካስረከቡ በኋላ በቀጣይም ለማዕከሉ የሚያደርጉትን እገዛና ድጋፍ እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል።

የከተማው ነዋሪዎችም በውጭ ሃገር ነዋሪ የሆኑት የአካባቢው ተወላጅ ሴት የዲያስፖራ አካላት በራሳቸው ተነሳስተው ለማህበረሠቡ በማሰብ ባስገነቡት በዚህ ማዕከል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በመቻላቸው መደሰታቸውን ገልፀው ለሴት ዲያስፖራ አከላቱ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>