Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

የቀብሪደሀር ቴ/ሙ/ት/ሥልጣና ኮሌጅ ደረጃ አረት ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን አስመረቀ

$
0
0

ቀብሪደሀር(Cakaaranews)ዕሮብ፤ሰኔ 06/2010ዓ.ም.በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀብሪደሀር ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጣና ኮሌጅ በ2007ዓ.ም ከተቋቋመ ጀምሮ በተለያዩ የስልጠና መስኮችን በመደበኛና አጫጭር ስልጠናዎች የሰለጠኑ  ተማሪዎችን አስመሪቆ ወደ ሥራ አሰማርቷል፡፡

ኮሌጁ የክልሉ ህብረተሰብ የሙያ ፊላጎት ለማርካት በተመለከተ በርካታ ገበያ ትኮር ጥናቶችን በማድረግ በገበያ ፊላጎት ያላቸው ሙያዎች የክልሉ ወጣቶችን አሰልጥኖ ወደ ገባያ አሰማርቷል፡፡ በዛሬ ዕለትም 63 መደበኛ ሰልጣኞችን እስከ ደረጃ አረት ብቃታቸው ከተረጋገጡ በኋላ የምረቃት ስነሥርዓት አደርጎላቸዋል፡፡

በምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ የተመራቂ ሰልጣኞችን ወላጆች፤የቆራሄይ ዞንና የቀብሪደሀር ከተማ መስተዳደር ኃላፊዎች፤ከተላያዩ የመንግስት ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረጉለት እንግዶችም ተገኝተዋል፡፡

በምረቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የቀብሪደሀር ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጣና ኮሌጅ ዲን አቶ አብድ ረሽድ  መሀመድ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸው ሲያስተላለፉ “በቅድሚያ ለዛሬው ተማራቂው ሰልጣኞችን  እንኳን ደስ አላችሁ እላቿለው ክቡራንና ክቡራት ለዚህ ቀን ለሶስተኛ ጊዜ የሚትመርቁ ተማሪዎች የኮሌጃችን ዋና አላማ ስላሳካችሁ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ እላለው”፤ በሃገራችን በየዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶቻችን ቀጣይነት በማረጋገጥና የበለጠ ውጤት በማስመዝገብ ሀገራችንን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍ የተነደፈው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በመተግበር ላይ ትገኛለች፤ ይህንን ተከትሎ የመጣውን ፈጣን ልማት ዘላቂነት ባለው መልኩ ለማሣደግ እና አገራዊ ራዕያችንን እውን ለማድረግ ብቁ የሰው ኃይል ማፍራት የማይተካ ድርሻ እንዳለው በሃገር ደረጃ ግንዛቤ ተይዞ የሰው ሀብታችንን አቅም ለማሳደግ፣ ፍትህ፣ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር በአስተማማኝ የሰፈነባትን ሀገር ለመገንባትና የያዝ ነው ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ የትምህርትና ሥልጠና ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው” ብሏል

በተጨማሪም የቆራሄይ ዞን ዋና አስተዳደሪ  አቶ አብዱልአዚዝ መሀመድ መልዕክታቸው ሲያስተላለፉ “በዛሬው ዕለት እዚህ ቦታ ተገኝቼ ለቀብሪደሀር ቴ/ሙ/ትና ስልጠና ኮሌጅ የሚያስመርቁት ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ  መልዕክተን ማስተላለፈን በጣም ተደስቻለው  ምክኒያቱም ተመራቂ ሰልጣኞችሁ ለክልላችን እድገት ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑን በመነሳት በበኩለ ደስ ብሎኛል” ሲሉ ተናግሯል፡፡

በሌላ በኩል የቀብሪደሀር ከተማ መስተዳደር ከንቲባ አቶ ዩሱፍ ሀሰን በቀብሪደሀር ቴ/ሙ/ት/ስልጠና ኮሌጅ   ለ3ኛ ጊዜ ካስመረቃቸው ሰልጣኞች መካከል ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ለተመረቁት ሰልጣኞችን የተለያዩ የማበረታቻ ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

በመጨረሻም ተመራቂ ሰልጣኞቹ ከብዙ ልፋት በኋላ ዛሬ ለዚህ ምርቃት በማብቃታቻውን በጣም መደሰተኛ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን በቀጣይም የተጣለባቸውን ሃላፊነት በአግባቡ እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>