ጅግጅጋ(Cakaaranews)ቅዳሜ፤ሰኔ 16/2010ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ከተመረጠ ወዲህ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሃገሪቱ በርካታ ስኬቶች፣ የብሔራዊ መግባባት እርምጃዎች እና ተግባራት እንደተፈጠሩ እርግጥ ነው።
ስለሆነም በራሴ በክልሉ መንግሥትና በክልሉ ህዝብ ሥም ልገልፅ የምፈልገው በአጭር ጊዜ ውስጥ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት በተገኙት አመርቂ እና ተጨባጭ የልማት ስኬቶች እንዲሁም ድሎች መመዝገብ በበኩሌ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ሲሉ ገልፀዋል።
በተጨማሪም በዛሬው እለት ሰኔ 16/2010 ዓ.ም ወይም እ.ኤ.አ ጁን 23/2018 በመዲናችን አዲስ አበባ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሃገሪቷ ህዝቦች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያላቸውን ደጋፊነት በሠላማዊ ሰልፍ ባሳዩበት አስደናቂ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተገኝተው ንግግራቸውን ባጠናቀቁበት ወቅት አሸባሪዎች በዜጎቻችን ላይ የሽብር ጥቃት ፈጽመዋል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት በራሱ በክልሉ መንግሥት እና በክልሉ ህዝብ ሥም ሲናገሩ ፍርሃት በተሞላበት መልኩ የአሻባሪ ቦምብ ጥቃት የፈጸሙትን አስፀያፊዎች ድርጊት እያውገዙ በጥቃቱ ለተጎዱ ወገኖቻችን፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የሃገራችን ህዝቦች የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ ፤ በጥቃቱ ለተጎዱት ዜጎቻችን በሚደረግ ድጋፍ ሁሉ የክልሉ መንግሥት በቀዳሚነት የበኩሉን እንደሚወጣ ክቡር ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።