Quantcast
Channel: Degaanka - Cakaara News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የ8ኛ ክፍል ሚንስተሪ ፈተና በጥሩ ሁኔታ መጀመሩ ተገለፀ

$
0
0

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ሰኞ፤ሰኔ 11/2010ዓ.ም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በሚገኙ 11 ዞኖች፣ 6 የከተማ አስተዳደሮችና 93 ወረዳወች የ8ኛ ክፍል ሚንስተሪ ፈተና በጥሩ ሁኔታ መጀመሩን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀረ።

ፈተናውን በክልሉ ከ33 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪወች እንደሚወስዱ በኢ.ሶ.ክ.የትምህርት ቢሮ ገልጿል። በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የ2010 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ በ547 ት/ቤቶች በተሳካ ሁኔታ ተጀምሯል።

በተጨማሪም የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ኢብራሂም አደም መሀድ ፈተናውን መጀመሩን አስመልክተው በጅግጅጋ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በመዘዋወር የፈተናውን ሂደት ጎበኝቷል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ኢብራሒም አደን "ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ ብሎም በክልላችን በሁሉም አካባቢዎች በተሳካ ሁኔታ የ8ኛ ክፍል ፈተና ተጀምሯል። በክልሉ በሚገኙ 11 ዞኖች፣ 6 የከተማ አስተዳደሮችና 93ወረዳዎች በሚገኙ 547 ት/ቤቶች ሚንስተሪ ብሔራዊ  ፈተናው ለ33,713 ተማሪዎች ይሰጣል፤በሠላምና በጥሩ ሁኔታ ይጠናቀቃል ብለንም እንጠብቃለን። በዚህም ለ3 ቀናት በሚቆየው ፈተና ላይ መላው የትምህርት አካላት ተማሪዎች፣ መምህራን እና ወላጆች እንዲሁም የክልል፣ የዞን፤የወረዳ አመራሮችና ባለሞያዎች ልክ እንደ 10ኛና 12ኛ ክፍል ፈተናዎች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አሁንም  የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲትወጡ እየጠየቅሁ ተማሪዎችም ፈተናውን በአግባቡ ተፈትነው እንዲያጠናቅቁ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ" ሲሉ ገልፀዋል።  

ከዚህ በተጨማሪም 2133 ፈታኞች፣ ተቆጣጣሪዎችና የፈተና ማዕከል አዛዦች በፈተናው ላይ እንደምሳተፉም ቢሮ ኃላፊው ገልፀዋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 131746

Trending Articles